Tender Detail

Tender Details

  • Deadline05 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-05 00:00:00
  • Categories Vehicle , Used Items

በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት በሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-/ሽያጭ/ 003/2017 የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች እና 004/2017 የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በሽያጭ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡


የጨረታ ማስታወቂያ

 

በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት በሽያጭ መለያ ቁጥር ሐረ-/ሽያጭ/ 003/2017 የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶች እና 004/2017 የተለያዩ ያገለገሉ ተሽከርካሪዎችን በሽያጭ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ሁሉ፡-

  1. ማንኛውም በጨረታው መካፈል የሚፈልግ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን 400 /አራት መቶ ብር/ በመክፈል ከመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 03 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  2. ተጫራቾች ለሚጫረቱባቸው ንብረቶች ለሚገዙት መነሻ ዋጋ 10% ለተሽከርካሪዎች 20% የሚሆነውን የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (Bid Bond) በባንክ በተረጋገጠ ቼክ /CPO/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ከሚያቀርቡት ከጨረታ ሰነድ ጋር በማያያዝ በፖስታ በማሸግ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ (የሚዘጋጀው /CPO/ በሐረሪ ህዝብ ክልላዊ መንግስት በመንግስት ግዥ እና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት ስም መሆን አለበት፡፡
  3. የጨረታ ሰነዱን የገዙ ተጫራቾች ለሽያጭ የተዘጋጁትን ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት በጨረታ ዶክመንት ውስጥ የተጠቀሰው መስሪያ ቤት ድረስ በመሄድ መመልከት ይችላሉ፡፡
  4. የጨረታ ሳጥኑ ሚያዝያ 27 እና 28 ቀን 2017 ዓ/ም ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ/ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአካል ባይገኙም ጨረታው በሰአቱ ይከፈታል፡፡
  5. በጨረታው የሚካፈለው ወኪል ከሆነ ሕጋዊ የውክልና ማስረጃ ማቅረብ ይኖርበታል፡፡
  6. የጨረታው አሸናፊ የሽያጭ ውል ከተዋዋለበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ቀናት ውስጥ ጠቅላላውን ክፍያ በመፈፀም ንብረቶችን ማንሳት ይኖርበታል፡፡
  7. የንብረቶች እና ተሽከርካሪዎችን መጓጓዣ ክፍያዎች በአሸናፊ ተጫራቾች የሚሸፈን ይሆናል፡፡
  8. መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው።

ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ፦

አድራሻ፦ ሐረር ከአራተኛ መስጂድ ወረድ ብሎ ዘቢዳ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 03

ስልክ ቁጥር፡- 025 6-66 00 37 ፋክስ፡- 0256590001

 

በሐረሪ ሕዝብ ክልላዊ መንግስት የመንግስት ግዥና ንብረት ማስወገድ አገልግሎት ሰጪ ጽ/ቤት

 

Save Tender