Tender Detail

Tender Details

  • Company Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-551-50-04
  • Websitehttps://combanketh.et/
  • Deadline22 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-22 00:00:00
  • Categories Steel, Metals And Aluminium , Machinery , Used Items

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሉሚኒየም ቁርጥራጮችን፣ የብረት ቁርጥራጮችን፣ የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖችን አካላትና አሮጌ ካዝናዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡

Commercial Bank of Ethiopia (የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ)


 

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ

COMMERCIAL BANK OF ETHIOΡΙΑ

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 007/2024/25

 

  1. የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የአሉሚኒየም ቁርጥራጮችን፣ የብረት ቁርጥራጮችን፣ የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖችን አካላትና አሮጌ ካዝናዎች ባሉበት ሁኔታ በጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ በብረት ማቅለጥ ዘርፍ ላይ የተሰማራ ፉብሪካ ብቻ ቀጥሎ የተዘረዘሩትን መመዘኛዎች አሟልቶ መገኘት ይኖርበታል፡፡
  2. ስለአሻሻጡ የተዘጋጀውን ዝርዝር ሁኔታ የያዘውን ሰነድ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 211 የማይመለስ ብር 300.00 (ሦስት መቶ ብር ብቻ) በመክፈል ከሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 12 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት መግዛት ይችላሉ፡፡
  3. ተጫራች ንብረቶቹን ከሚያዝያ 14 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ እስከ ግንቦት 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቃሊቲ ቅርንጫፍ ትይዩ ባለው አስፓልት ወደ ውስጥ ገባ ብሎ በሚገኘው የቀድሞ ብራሌ ጥጥ መዳመጫ ግቢ ውስጥ ከጠዋቱ ከ2፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 6፡00 ሰዓት ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 7፡00 ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ባሉት የስራ ቀናት በመገኘት ማየት ይችላል፡፡
  4. የአሉሚኒየም ቁርጥራጮችን፣ የብረት ቁርጥራጮችን፤ የአውቶማቲክ ገንዘብ መክፈያ ማሽኖች አካላትና አሮጌ ካዝናዎች ጨረታ ለመሳተፍ በብረት አቅላጭ ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ፉብሪካዎች ከማዕድን ሚኒስቴር የብረት ድልድል ተጠቃሚ እንዲሆን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል ብቻ መሆን አለበት፡፡
  5. የተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት ላይ ታዛቢዎች በተገኙበት ይታሸጋል፡፡
  6. ተጫራች ለንብረቱ የሚሰጠውን ዋጋ ከጨረታ ሰነዱ ላይባለው ክፍት ቦታ በመሙላት የጨረታ ማስከበሪያ እና ሌሎችም አስፈላጊ ሰነዶችን በፖስታ በማሸግ ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሕንፃ 2ኛፎቅ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማስገቢያ ሳጥን ውስጥ ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 3:00 ሰዓት እስከ 4፡00 ሰዓት ብቻ ያስገባል፡፡
  7. ግንቦት 14 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው እንዲሁም ታዛቢዎች በተገኙበት ቄራ ፊት ለፊት በሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሠራተኞች የመዝናኛ ክበብ አዳራሽ ውስጥ በግልጽ ይከፈታል፡፡
  8. ተጫራች ለሚጫረትበት ንብረቶች 150,000.00 (አንድ መቶ አምሳ ሺ) የጨረታ ማስከበሪያ (Bid Bond) በባንክ ክፍያ ማዘዣ (CPO) ለኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለያገለገሉ ንብረቶች አስወጋጅ  (Commercial Bank of Ethiopia Disposal) በሚል ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ለጨረታ ማስከበሪያ የተያዘው ሲፒኦ አሸናፊ ለሚሆነው በሚገዛው ንብረት ክፍያ ላይ የሚታሰብ ሲሆን አሸናፊ ላልሆኑት ለጨረታ ማስከበሪያ ያስያዙት ሲፒኦ ተመላሽ ይደረግላቸዋል፡፡

 

ባንኩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

 

Save Tender