የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በቅጥር ግቢው ውስጥ በ360 ካ.ሜ ቦታ ላይ የB+G+2+T ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል:: ስለሆነም ቤተክርስቲያኗ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ዝርዝር መስፈርት የሚያሟሉ ልጆቿ በጨረታው እንዲሳተፉ ትጋብዛለች ::
ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ አስተዳደር ጽ/ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የግንባታ ጨረታ
በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ
አሜን !!!
የደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ሰበካ ጉባኤ ጽ/ቤት በቅጥር ግቢው ውስጥ በ360 ካ.ሜ ቦታ ላይ የB+G+2+T ለተለያዩ አገልግሎት የሚውል ሕንጻ ለመገንባት ዝግጅቱን አጠናቋል:: ስለሆነም ቤተክርስቲያኗ ከዚህ በታች የተቀመጠውን ዝርዝር መስፈርት የሚያሟሉ ልጆቿ በጨረታው እንዲሳተፉ ትጋብዛለች ::
- በዚህ መሰረት ተጫራቾች፡-
1ኛ. ደረጃ 5 BC / ደረጃ 5 GC ሥራ ተቋራጭ እና ከዚያ በላይ መሆን አለባቸው::
2ኛ. የታደሰ ንግድ ፍቃድ ፤ ተ.እ.ታ ስርተፊኬት ፤ የቲን ሰርተፊኬት (TIN) ፤ በጨረታ መሳተፍ የሚያስችል ስለግብር አከፋፈል የሚሰጥ ማስረጃ (Tax clearance certificate) ፤ የሙያ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ እና FPPA የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
3ኛ. የጨረታ ማስከበሪያ የብር 200,000 CPO ወይም Unconditional bank guarantee ማስያዝ አለባቸው ::
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በሪፖርተር ጋዜጣ ከወጣበት ሚያዚያ 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም አየር ላይ ይውላል::
- ጨረታው ሚያዚያ 25 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡30 ተዘግቶ በዚሁ ቀን ከጠዋቱ 5፡00 ተጫራቾች ባሉበት የሚከፈት ይሆናል::
- የጨረታ ሰነድ መውሰጃ እና መመለሻ (ማስገቢያ) ቦታ በቤተክርስቲያኗ ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 001 ነው::
- የጨረታው ዝርዝር መስፈርት እና መመሪያ ከጨረታው ሰነድ ላይ ማግኘት ይቻላል::
- ተጫራቾች በጨረታው ሰነድ ላይ የተቀመጠውን መስፈርት የሚያሟሉ መሆን አለባቸው ::
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 1.000 በመክፈል ከታች በተጠቀሰው አድራሻ መውሰድ ይቻላል::
➢ ቤተክርስቲያኗ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ ለሙሉ በማንኛውም ጊዜ የመሰረዝ መብቷ የተጠበቀ ነው::
➢ አድራሻ፡-
አዲስ አበባ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ
ወረዳ 01 በመርካቶ አከባቢ
ደብረ ኃይል ቅዱስ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ ቢሮ ቁጥር 001
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር
0911 43 83 71 / 0946 55 27 27 / 0911 14 68 03
