Tender Detail

Tender Details

  • Company በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት
  • Address ኢትዮጵያ, Phone: 0587600018
  • Website
  • Deadline05 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-05 00:00:00
  • Categories Building Materials , Office Supplies And Services , Water Pipes And Fittings

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2017 በጀት በ4ኛ ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የፅዳት እቃዎችን፤ በሎት 2 የተለያዩ ቀላል የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ በሎት 3 የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን እንዲሁም በሎት 4 የተለያዩ የቧንቧ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በትምህርትና ሥልጠና ዋና መምሪያ የብር ሸለቆ መሠረታዊ ውትድርና ማሠልጠኛ ትምህርት ቤት


 

ግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር በስልጠና ዋና መምሪያ የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማሰልጠኛ ትምህርት ቤት በ2017 በጀት በ4ኛ ሩብ ዓመት በሎት 1 የተለያዩ የፅዳት እቃዎችን፤ በሎት 2 የተለያዩ ቀላል የቢሮ መገልገያ እቃዎች፣ በሎት 3 የተለያዩ የግንባታ እቃዎችን እንዲሁም በሎት 4 የተለያዩ የቧንቧ እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

ተጫራች ማሟላት የሚገባቸው

  1. ተጫራች በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  4. የግብር ከፋይ ምዝገባ (ቲን ነምበር) ማቅረብ የሚችል፤
  5. የዘመኑ ግብር የከፈለበት /ከኢትዮ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን/ በጨረታ ለመሳተፍ የተሰጠው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤
  6. ተወካይ ከሆነ /ከሆነች⁄ ህጋዊ የውከልና ማስረጃ ማቅረብ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  7. ተጫራቾች በዋጋ ማቅረቢያው ሰነድ ላይ የድርጅቱን ማህተምና ፊርማ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡
  8. ዋጋ ሲሞሉ የአንዱን ዋጋ ቫት ሳይጨምር በመሙላት በዘርፋ ድምር ከተሰራ በኋላ የቫት ድምር ለብቻ መቀመጥ አለበት፡፡
  9. ተጫራች የአንዱን ዋጋ ከሞላ በኋላ የጠቅላላ ድምር ወደ ጎንም ወደ ታችም ደምሮ ማስቀመጥ ይኖርበታል።
  10. በጨረታ አሸናፊ የሚለየው በተቀመጠው የዕቃ ዝርዝር በተናጠል ዝቀተኛ ዋጋ ያቀረበ ተጫራች አሸናፊ የሆነ ይመረጣል፤
  11. በሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ መኖር የለበትም እንዲሁም በሰነዱ ላይ ፍሉድ ከተጠቀሙ ሰነዱ ከውድድር ውጪ ይሆናል፡፡
  12. ተጫራቹ የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ሲያቀርቡ ኦርጅናልና ኮፒ ብለው መለየት ይኖርባቸዋል፡፡ ኦርጅናሉን ፋይናንሻል ለብቻ ኮፒውን ፋይናንሻል ለብቻ በማሸግ እንዲሁም በየዘርፉ ከተራ ቁጥር 1-6 የተዘረዘሩትን ማስረጃዎች ለብቻው በአንድ ፖስታ በማሸግና በመጨረሻ ሶስቱንም ፖስታዎች በአንድ ትልቅ ፖስታ አሽጎ የሚወዳደርበትን ዘርፍ በመፃፍ ማቅረብ አለበት። ስለሆነም በዚህ መሰረት ሶስቱንም ፖስታዎች ሳያሽግ በአንድ ላይ አሽጎ ቢመጣ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡
  13. ተጫራች ለጨረታ ማስከበሪያ ባቀረቡት ዋጋ ከ 2% በጥሬ ገንዘብ ወይም በC.P.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  14. የጨረታ አሸናፊ ለውል ማስከበሪያ ካሸነፈው ጠቅላላ ዋጋ ልክ 10% በጥሬ ገንዘብ ወይም በCP.O ማስያዝ የሚችል መሆን አለበት፡፡
  15. የጨረታ ሰነዱን ከማሰልጠኛ ት/ቤቱ ፋይናንስ ዴስክ በስራ ቀንና ሰዓት ከ12/8/2017ዓ/ም ጀምሮ እስከ 26/8/2017 ዓ/ም ድረስ የሚጫረቱበትን የጨረቻ ሰነድ 100 (እንድ መቶ ብር) በመክፈል መውሰድ ይችላሉ፡፡
  16. ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሰነዳቸውን በ27/8/2017 ዓ/ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ 7፡00 ሰዓት ድረስ በማ/ት/ቤቱ ቢሮ በር ላይ በሚዘጋጀው ሳጥን ሰነዱን ማስገባት አለባቸው። በዚሁ ቀን 27/8/2017 ዓ/ም ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙብት በማ/ት/ቤቱ መሰብሰቢያ አዳራሽ ከቀኑ 7:30 ላዶ ጨረታው ይከፈታል፡፡
  17. አሸናፊ የሆነው ተጫራች ማ/ት/ቤቱ በሚሰጠው የአቅርቦት ትዕዛዝ መሰረት ጥራቱን በጠበቀ መንገድ ዕቃውን አሟልቶ ማቅረብ የሚችል እና በማ/ት/ቤቱ የጥራት ኮሚቴ ተረጋግጦ ካልተቀበለው እቃውን ቀይሮ የማምጣት ግዴታ አለበት፡፡
  18. አሸናፊ የሆነው ነጋዴ ከፍያ በሚጠይቅበት ጊዜ ህጋዊ ደረሰኝ ከካሽ ሬጅስተር ጋር አያይዞ ማቅረብ አለበት። ይህን ማቅረብ የማይችል ከሆነ ምንም ዓይነት ከፍያ መጠየቅ አይችልም፣ ማ/ት/ቤቱም እንዲከፍል አይገደድም።
  19. ማ/ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው።
  20. ጨረታውን አሸናፊ ከሆነ ድርጅት ማ/ት/ቤቱ በጀቱን በማረጋገጥ በዘርፉ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው::
  21. በዚህ ማስታወቂያ ያልተገለፁ ሌሎች ህጎች በሀገሪቱ የግዥ አፈፃፀም መምሪያ መሰረት ተፈፃሚነት ይኖራቸዋል፡፡ ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 0587600018 በስራ ሰዓት ደውሎ ማረጋገጥ ይችላሉ።

 

በሀገር መከላከያ ሚኒስቴር የብርሸለቆ መሰረታዊ ውትድርና ማ/ት/ቤት

 

Save Tender