የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ያገለገሉ ዕቃዎችን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
በድጋሚ የወጣ የጨረታ
ማስታወቂያ
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር በ2017 በጀት ዓመት ያገለገሉ ዕቃዎችን በድጋሚ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን የሚመለስ ብር 1,000.00 (አንድ ሺህ) በሲፒኦ በማስያዝ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ በ15 የሰራ ቀን ውስጥ የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ ዋስትና አስተዳደር ቢሮ ቁጥር 01 በአካል በመቅረብ የማይመለስ ብር 100 (መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነዱን መግዛት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡ ጨረታው የሚከፈተው የጨረታው ማስታወቂያ በወጣበት በ16ኛው ቀን ከሰዓት በኋላ ልክ 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን በ8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
አድራሻ 4 ኪሎ ወደ መገናኛ በሚወስደው መንገድ ህፃናትና ወጣቶች ቲያትር ፊት ለፊት በስልክ ቁጥር 0111232705 ደውለው ተጨማሪ መረጃ ማግኘት የሚትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
ማሳሰቢያ፤ ተጫራቾች ለምትወዳደሩበት ዕቃ ለእያንዳንዱ ዋጋ መሞላት አለበት ::
አስተዳደሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
የመንግስት ሰራተኞች ማህበራዊ
ዋስትና አስተዳደር
