የወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለ2017 በጀት ዓመት ለጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ዓመታዊ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
Wolaita TV (ወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ)
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር ወቴቪ 001/2017
የወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለ2017 በጀት ዓመት ለጣቢያው አገልግሎት የሚውሉ ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች ዓመታዊ ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ተጫራቾች ፡-
- በየዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ፣ የምዝገባ ምስክር ወረቀት ፣የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ሰርተፊኬት እና የታክስ ከፋይነት ማረጋገጫ (ቲን) ማቅረብ አለባቸው፡፡
- የእቃ አገልግሎት አቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት በማያያዝ ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ/ ብር በየለቱ እየከፈሉ ከወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 06 የጨረታውን ዝርዝር መግለጫ የያዘ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ብር 30,000 /ሠላሳ ሺህ/ ብር በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ የጨረታ ሀሳብ ሰነድ ጋር አሽገው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች አንዱን ዕቃ የሚያቀርቡትን የመወዳደሪያ ሀሳባቸውን በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ በጨረታ ሰነድ ላይ በተዘጋጀው የዋጋ መሙያ ሠንጠረዥ በመሙላት በወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን በጨረታ አዳራሽ ቢሮ ቁጥር 08 መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የሚቆጠር ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት አየር ላይ ውሎ በ16ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዕለቱ በ4፡30 ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጣቢያው የጨረታ አዳራሽ ይከፈታል።
- 16ኛው ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፏቸውን ዕቃዎች አስፈላጊውን ውለታ በመፈጸም ሙሉ በሙሉ በወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ ድረስ በማቅረብ ገቢ ሲያደርጉ ክፍያ የሚፈጸም ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነድ አንድ ኦርጅናል እና አንድ ኮፒ ተዘጋጅቶ በጨረታ ሣጥን ውስጥ በዕለቱ መጨመር ይጠበቅባቸዋል።
- ለተጨማሪ መረጃ ስልክ 0461802871 ደውሎ መጠየቅ ይችላሉ።
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ወላይታ ቴሌቪዥን ጣቢያ
