Tender Detail

Tender Details

  • Company በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ኬራቴ ከተማ ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09-11-66-04-91
  • Website
  • Deadline02 May 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-05-03 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በካፒታል በጀት ለሁልባራግ ወረዳ ሻማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውሉ ABC ኬብል /5,000 ሜትር 3*50mm2+35mm2/ እና ትራንስፎርመር ባለ200 KVA እና ባለ100 KVA በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል መንግሥት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በካፒታል በጀት ለሁልባራግ ወረዳ ሻማ ማዘጋጃ ቤት አገልግሎት የሚውል፡-

  1. ABC ኬብል /5,000 ሜትር 3*50mm2+35mm2/
  2. ትራንስፎርመር ባለ200 KVA እና ባለ100 KVA በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ፡-

  1. በመስኩ የታደሰ የንግድ ፍቃድ እና የስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል፤
  2. የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ
  3. የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ ሰርተፍኬት የሚያቀርብ፤
  4. በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ የአቅራቢነት ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
  5. የዘመኑን ግብር አጠናቀው ስለመክፈላቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ
  6. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለሎት 01/ኬብል/ብር 30,000 /ሰላሳ ሺህ ብር/ እና ለሎት 02 ትራንስፎርመር /80,000 /ሰማኒያ ሺህ/ ብር እውቅና ባለው ባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ማቅረብ የሚችል።
  7. ተጫራቾች በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተገለጸው መሰረት እቃዎቹን ማሸነፋቸው ከተገለጸላቸውና የውል ስምምነት ከተፈራረሙ በኋላ እቃዎቹን ሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መጋዘን ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
  8. ትራንስፎርመር ለመግዛት የሚያስፈልጋቸውን ቴክኒካል እስፔስፊኬሽን guaranteed technical particulars specification /G.T.P/ የተሰጠን መሆኑን እየገለጽን ትራንስፎርመሩ በተሰጠው ቴክኒካል እስፔስፊኬሽን መሰረት ተገዝቶ የቀረበ መሆኑንና በኢትዮጵያ ኤሌክትሪካል አገልግሎት እንካ ሪሰርችና ዴቨሎፕመንት ቢሮ በኩል የጥራት ደረጃው በላቦራቶሪ ፍተሻ ተረጋግጦ መስፈርቱን ሲያሟላ ብቻ ክፍያ የሚፈፀም መሆኑን እናሳውቃለን።

ተጫራቾች የጨረታ ሰነድ በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን በሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 04 በአካል በተወካይ አማካይነት የማይመለስ ብር ለሎት አንድ /ኬብል) 500 (አምስት መቶ ብር) እና ለሎት ሁለት ትራንስፎርመር/ 500 (አምስት መቶ ብር) በመከፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላል። ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በታሸገው ኤንቨሎፕ በማድረግ ይህ ማስታወቂያ 15 ተከታታይ ቀናት ሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ማስገባት ይጠብቅባቸዋል። የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው ከወጣ ታሽጎ 9፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት ጀምሮ ባሉት ቁጥር 04 ለዚህ ባዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ከ15ኛው ቀን በኋላ ባለው የስራ ቀን 8፡30 ሰዓት በተገኙበት በግልጽ ይከፈታል።

ማሳሰቢያ

ተጫራቾች ያቀረቡት የጨረታ ዋስትና ከተጠየቀው ዋጋ አንሶ ከተገኘ ከጨረታው ይሰረዛሉ።

የተወዳዳሪ አቅራቢ ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው አለመገኘት የጨረታ መከፈቻ ቀኑን አይለውጠውም።

ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 09 11 66 04 91/ 09 21 00 11 67 ይደውሉ

 

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት በስልጤ ዞን የሁልባራግ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
MSF Belgium Ethiopia Mission Tender for Supply of Various Types of Stabilizers (Tender Ref. ET121 &...

READ MORE