ሕይወት ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ስር የሚተዳደረው 04 ቀበሌ ምስራች መዝናኛ ክበብ የ2016ዓ.ም የአንድ ዓመት የሂሳብ ስራዎችን የሚያሳይ ኦዲት የግልፅ ጨረታ በማውጣት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
ሕይወት ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር
የመዝናኛ ክበባትን ኦዲት ለማድረግ የወጣ
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
ሕይወት ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር ስር የሚተዳደረው 04 ቀበሌ ምስራች መዝናኛ ክበብ የ2016ዓ.ም የአንድ ዓመት የሂሳብ ስራዎችን የሚያሳይ ኦዲት የግልፅ ጨረታ በማውጣት ኦዲት ማስደረግ ይፈልጋል።
በመሆኑም በኦዲተርነት የሙያ መስክ መስፈርቱን የምታሟሉ ተወዳዳሪዎች እንድትወዳደሩ በግልፅ ጨረታ የጋበዝን መሆናችንን እየገለፅን ለመወዳደር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፡-
- የዘመኑ የታደሰ ፍቃድ ያለው
- የታደሰ የስራ ንግድ ፍቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው
- የዘመኑን ግብር የከፈለ
- ለመንግስት የሚጠበቅበትን ግብር የከፈለ
- ከዚህ በፊት በኦዲት ሙያ ተሰማርቶ የነበረ እና የስራ አፈፃፀም የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል
- በኢትዮጵያ ኦዲት ቦርድ በኦንላይን ዝርዝር ውስጥ የተመዘገበ ለመሆኑ ማስረጃ ማቅረብ የሚችል
- የሚጫረቱበትን 2% የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም በባንክ የተረጋገ ጋራንቲ ማስያዝ የሚችሉ
- ጨረታውን ካሸነፉ የውል ማስከበሪያ 10% CPO ወይም በባንክ የተረጋገጠ ጋራንት ማስያዝ የሚችሉ
- የጨረታ ሰነድ የማይመለስ 100.00 ብር በመክፈል መግዛት የሚችል እና የማህበሩ ስራ አመራር ኮሚቴ በሚያቀርበው የውል ሰነድ ህጋዊ የውል ስምምነት መዋዋል የሚችል ሆኖ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ10 ተከታታይ የስራ ቀናቶች ውስጥ የጨረታ ሰነዱን በሕይወት ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማ/ ጽ/ቤት በመግዛት መጫረት የሚችሉ መሆኑን እናሳውቃለን።
- የኦዲቱ ስራ እንደተጠናቀቀ ሪፖርቱን ለጉ/ክ/ ከተማ ህብረት ስራ ኦዲት ቡድን አቅርቦ ካስተቸ ካስገመገመ በኋላ ለአመራር ቦርዱ የሚያርቡ ለጠቅላላ ጉባኤ ቀርቦ ለማንበብና ለማስረዳት ፈቃደኛ የሆነ
ማሳሰቢያ፡-
ማህበሩ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። -
የሥራ ቀናት ቅዳሜ ግማሽ ቀንን ይጨምራል።
አድራሻ ፡- ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 አስተዳደር ጊቢ ውስጥ የሸማች ዋና ጽ/ቤት
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 09 22 33 93 38 ይደውሉ።
ሕይወት ሸማቾች ኃ/የተ/የህ/ስ/ማህበር
