ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ሰነድ ቁጥር ግ/ላ/ኢ/04/2017
ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎችን ባሉበት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ሎት 1፡ ከ 2-7 ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 20 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ቴንድኖ ብረት
ሎት 2፡ ከ 2 ሜትር በታች የተቆራረጡ ከ6-20 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር የሆኑ ቴንድኖ ብረቶች
ሎት 3፡ ባለ 28 ጌጅ 3 ሜትር ርዝመት ያለው የጣራ ቆርቆሮ
ሎት 4፡ ባለ 28 ጌጅ 5 ሜትር ርዝመት ያለው የጣራ ቆርቆሮ
ሎት 5፡ አገልግሎት የሠጠ የላሜራ በር
ሎት 6፡ ያገለገለ ተደራራቢ የብረት አልጋ
ሎት 7፡ የብረት ፓኔል
ሎት 8፡ አገልግሎት የሠጡ የፕላስቲክና የጎማ አይነቶች
ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ።
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ አለባቸው ድርጅት ከሆነ በድርጅቱ ስም መመዝገብ ይኖርበታል።
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኘው የግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 1 በመሄድ ብር 400 (አራት መቶ ብር ) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ቡና ባንክ (አዲስ አበባ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ፣ ባህርዳር፣ ባህርዳር (ጊዮርጊስ አካባቢ) ቅርንጫፍ፣ ደሴ፣ ጦሳ ቅርንጫፍ በመሄድ በግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ቡና ባንክ ሂሳብ ቁጥር 15596001000213 ገቢ በማድረግ ከደረሰኝ ጋር መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ የዋጋ መሙያና የጨረታ ሰነድ የገዙበትን የባንክ አድቫይሥ (ደረሰኝ) በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ ዶክመንት ለየብቻው አድርገው በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም (የተከለከለ ነው)፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 3 የተገለፁትን አሟልተው ከተገኙ የሚወዳደሩት በሞሎት ነጠላ ዋጋ ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍለው እስከሚወስዱ ድረስ ለውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በሚረከበው የዕቃ መጠን ክፍያ እየፈጸመ ንብረቶቹን ውል በያዘ በ20 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የእቃውን የሚዛን፤ የጫኝ አውራጅና ትራንስፖርት ወጭ በራሱ ይሸፍናል።
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማንኛውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09-20-47-80-39 ወይም 09-13-07-25-07 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
ወልዲያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ
