Tender Detail

Tender Details


የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ኢንተርፕራይዙ ለሚያስገነባቸው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች አቅርቦትና ስራ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

Menkorer Construction Enterprize (የመንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ)


 

ብሔራዊ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ

 

የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት በአማራ ክልል በምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የሚገኝ መንግስታዊ የሆነ የልማት ድርጅት ሲሆን ኢንተርፕራይዙ ለሚያስገነባቸው ለተለያዩ ፕሮጀክቶች ግንባታ አገልግሎት የሚውል ዕቃዎች አቅርቦትና ስራ ከዚህ በታች በተቀመጠው ዝርዝር መሰረት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡

  • ምድብ 1 ለጅ +10 ደ/ማ አልማ ህንፃ ግንባታ የሴራሚክ አቅርቦት
  • ምድብ 2 ለደ/ማርቆስ ጠቅላላ ሆስፒታል ፖርሲሊን ፍሎር ታይል፣ ማርብል ችፕስ፤ ቴራዞ ስከርቲንግ እና ፎርሲሊንግ ስካርቲንግ አቅርቦት
  • ምድብ 3 ለደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል ፖርሲለን ፍሎር፣ ማርብል ችፕስ፣ ቴራዞ ስከርቲንግ እና ፎርሲሊንግ ስካርቲንግ አቅርቦት
  • ምድብ 4 ለጅ+10 ደ/ማ አልማ ህንፃ ግንባታ ክሊንከር ወል ታይል አቅርቦትና ገጠማ
  • ምድብ 5 ለጅ+10 ደ/ማ አልማ ህንፃ ግንባታ ስቶን ክላዲንክ አቅርቦትና ገጠማ
  • ምድብ 6 ለፍኖተ ሰላም አርቲሲ የእንጨት በር አቅርቦትና ገጠማ
  • ምድብ 7 ለፍኖተ ሰላም አርቲሲ መስታዎት አቅርቦትና ገጠማ
  • ምድብ 8 ለደ/ብርሃን ጠቅላላ ሆስፒታል መስታዎት አቅርቦትና ገጠማ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ማስቀረብና ማሰራት ይፈልጋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-

      1. ተጫራቾች የምትጫረቱበትን ሰነድ ያንዱን ዋጋ በመሙላት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 /አስራ አምስት/ ቀናት በድርጅቱ ቢሮ ቁጥር 7 ማስገባት አለባችሁ፡፡
      2. ጨረታው የጨረታ ማስገቢያው በተጠናቀቀ በቀጣይ ቀን ከጠዋቱ 3፡00 ታሽጎ 3፡30 ላይ ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፣ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ በበአላት ቀን ከሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ሆኖም በራሳቸው ፈቃድ በመክፈቻው ቀን ባይገኙ የጨረታውን መከፈት አያግደውም፡፡
      3. ተጫራቾች በዘርፉ ህጋዊ የተመዘገበና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የነጋዴነት መለያ ቁጥር፣ የዘመኑን ግብር የነበሩና የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው::
      4. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ደ/ማርቆስ ከተማ በሚገኘው መንቆረር ኮንስትራክሽን ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 11 ድረስ በመቅረብ ብር 200 በመክፈል መውሰድ ይችላሉ።
      5. በየምድባቸው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ፋይናንሻል ኦርጅናል እና ኮፒ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው::
      6. አሸናፊው ድርጅት ከምድብ 4 እስከ ምድብ 8 ያሉ ዕቃዎችን በየፕሮጀክቱ በራሱ ትራንስፖርት በማቅረብ እና ገጥሞ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
      7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ የጠ/ዋጋ 2% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለባቸው::
      8. አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርባቸው እቃዎች እና ስራ በባለሙያ ወይም ቴስት ተረጋግጦ ማለፍ አለበት።
      9. አሸናፊው የሚለየው በየምድባቸው በሎት ወይም በጥቅል ይሆናል፡፡
      10. አሸናፊው ድርጅት የውል ማስከበሪያ 10% በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና፣ የመድን ዋስትና ወይም በሲፒኦ ማስያዝ አለበት፡፡
      11. ተጫራቾች አሸናፊ መሆናቸው ከተገለፀላቸው ባሉት 7 /ሰባት/ የሥራ ቀናት ውስጥ ውል ይዘው ወደ ሥራ መግባት አለባቸው::
      12. አሸናፊው ድርጅት 1-3 ያሉ ምድቦች አቅርቦቶችን በአማካሪ መሃንዲስ ድርጅት ሳንፕል አፅድቆ በየፕሮጀክቱ ማቅረብ ይጠበቅበታል፡፡
      13. በምድብ 4 እና 5 የሚወዳደሩ ተጫራቾች ከታወቀ ድርጅት 2 እና ከዚያ በላይ መልካም ሥራ አፈፃፀም የማቅረብ ግዴታ አለባቸው፡፡
      14. ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ወይም አማራጭ ካገኘ በከፊልም ሆነ በሙሉ ጨረታውን የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0930958351 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በደብረማርቆስ ከተማ አስተዳደር የመንቆረር ኮንስትራክሽን ድርጅት

 

Save Tender