Tender Detail

Tender Details

  • Company የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር
  • Address ፒያሣ የቀድሞ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ዋና ጽ/ቤት የነበረ በስተጀርባ በሚገኘው የድርጅቱ ጽ/ቤት : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0911 80 48 20
  • Website
  • Deadline22 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-22 00:00:00
  • Categories Textile, Garment & Leather , Cloth And Shoes

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክስዮን ማኅበር ቀጥሎ የተመለከተውን መስፈርት ከሚያሟሉ ተጫራቾች ለጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች የተሰፋ የደንብ ልብስ ሱሪና ሸሚዝ አርማ ያለው፤ የዝናብ ልብስ እና ጃኬት ካራቫት መለዮ የወንድ ከስክስ ጫማ የሴቶች ጉርድ ጫማ ፤ ለጽዳት ሠራተኞች ጋዎን በጀርባ ላይ አርማ ያለው በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክስዮን ማኅበር ቀጥሎ የተመለከተውን መስፈርት ከሚያሟሉ ተጫራቾች ለጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች የተሰፋ የደንብ ልብስ ሱሪና ሸሚዝ አርማ ያለው፤ የዝናብ ልብስ እና ጃኬት ካራቫት መለዮ የወንድ ከስክስ ጫማ የሴቶች ጉርድ ጫማ ፤ ለጽዳት ሠራተኞች ጋዎን በጀርባ ላይ አርማ ያለው በጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በዚሁ መሰረት፡-

1ኛ/ በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ የንግድና ሥራ ፈቃድ ያለው ሆኖ የዘመኑን ግብር የከፈለ ስለመሆኑ የከፈለበትን ኮፒ ማቅረብ የሚችል፣

2ኛ/ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN)፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ (ቫት) ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

3ኛ/ ተጫራቶች የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ (CPO) የዋጋዉን 10% ማስያዝ አለባቸው::

4ኛ/ የጨረታ መወዳደሪያ ዝርዝር መግለጫ (Technical) ኦርጂናል እና ኮፒ ሁለት ፖስታ እንደዚሁም የፋይናንሻል በአንድ ፖስታ በማድረግ እንደዚሁም ሲፒኦ (CPO) በአንድ ፖስታ በማድረግ እና ሁሉንም በአንድ ፖስታ በማጠቃለል በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት አለባቸው፡፡

5ኛ/ ለጨረታ የተዘጋጀውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 6ኛው ቀን የማይመለስ ብር 200 በመክፈል ዘወትር በሥራ ሰዓት ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡

6ኛ/ በጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈውን የደንብ ልብስም ሆነ ጫማ በራሱ ትራንስፖርት ሸገርከተማ በቡራዩ ቴሌኮም ቢሮ 3ኛ ፎቅ የአክስዮን ማህበሩ ቁጥር 2 ቢሮ ወስዶ ያስረከባል፡፡

7ኛ/ ተጫራቾች ለሚወዳደሩበት የደንብ ልብስ እና ጫማ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ የጨርቁ መልክና ዓይነት ከአሸናፈው ድርጅት ጋር በውል ጊዜ የሚወሰን ይሆናል ፡፡

8ኛ/ ለጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች የተሰፋ ሸሚዝና ሱሪ የድንብ ልብስ በሸሚዝ የደረት ኪስና መለዮ ላይ እንደዚሁም በጽዳት ሠራተኞች ጋዎን ጀርባ ላይ የድርጅቱን ዓርማና ስም ህትመት ይደረግበታል፡፡

9ኛ/ ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ7ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡

10ኛ/ ድርጅቱ ሌላ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::

 

አድራሻችን፡- 22 ማዞሪያ ኦሮሚያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ኮርድኔሽን ሥራ አስፈፃሚ ጽ/ቤት

በነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት አ/ማ/ሠራተኞች ጽ/ቤት ይሆናል፡፡

ስልክ ቁጥር 0911 80 48 20/09 12 03 74 86

 

የነገ ተስፋ ጥበቃና ጽዳት ሠራተኞች አክሲዮን ማህበር

 

Save Tender