የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መገዛት ይፈልጋል ::
የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን በ2017 በጀት ዓመት ለሆስፒታሉ አገልግሎት የሚውሉ
- ደንብ ልብስ
- የተለያዩ የጽህፈት መሳሪያ
- የተለያዩ ህትመቶችን
- የተለያየ የጽዳት እቃዎች
- የተለያዩ የመኪና መለዋወጫ እቃዎች
- የተለያዩ ፕላንትና ማሽነሪዎች
- ፈርኒቸሮችን
በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መገዛት ይፈልጋል ::
በዚህም መሰረት :-
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር (TIN) ያለው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /ቫት ተመዝጋቢ የሆኑ
- ተጫራቾች ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ የማይመለስ ፎቶ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታ ሰነዱን ሲገዙ ለእያንዳንዱ የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200 በመክፈል በሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 96 ድረስ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 2% በባንከ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይኖርባቸዋል።
- የጨረታ ሰነዱን ዋና እና ቅጅ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ ግዥ ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 96 ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማስገባት ይኖርባቸዋል።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን ከጨረታው ውድድር ማግለል አይችልም።
- ማንኛውም ተጫራች ጨረታው ከተከፈተ በኋላ ራሱን በጨረታ ሰነዱ የሰጠውን ዋጋና መግሎጫ መለወጥና ማሻሻል አይችልም።
- ጨረታው በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ በ4:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል (ባይገኙም ይከፈታል)፣ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣይ የስራ ቀን ይፈጸማል።
- አሸናፊው የሚለየው በነጠላ ዋጋ ወይም በሎት ጠቅላላ ድምር ስለሚሆን ሁሉንም መሙላት ይኖርበታል።
- ሆስፒታሉ እንደበጀቱ ሁኔታ በጨረታ ሰነዱ ላይ የተዘረዘሩትን እቃዎች ብዛት መጨመርም ሆነ መቀነስ ይችላል።
- አሸናፊው ድርጅት የሚቀርቡትን እቃዎች ጥራታቸውን ጠብቆ ሀይቅ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል አቅርቦ እንዳጠናቀቀ ገንዘቡን ወጭ አድርጎ ይወሰዳል።
- የሚገዙት እቃዎች ጥራታቸውን የጠበቁ መሆን አለባቸው።
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው ::
- ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር 033-822-06-78 /0913808243 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል።
በአ/ብ/ክ/መ/ጤና ጥበቃ ቢሮ /በደ/ወሎ/ዞ/የሀይቅ መጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል
