መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሶዶ ቅ/ፅ/ቤት
ብሔራዊ ግልጽ የጨረታ
ማስታወቂያ የጨረታ ቁጥር፡-ሶዶ/ግ/ጨ/001/2017
መ/ቤታችን በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች በሠንጠረዥ የተመለከቱትን ከመንግሥት በተፈቀደለት በጀትና በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ የግዥ ዘዴ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
|
ተ.ቁ |
የግዥው ዓይነት መግለጫ |
የጨረታ ሠነዱ መግዥያ ዋጋ (የማይመለስ) |
የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ ወይም የባንክ ዋስትና መጠን በብር |
|
1 |
የቢሮ ኪራይ ጨረታ ለሁለት አመት የሚቆይ |
100.00 |
5,000.00 |
በመሆኑም ተጫራቾች፡-
- የጨረታ ሰነዱን የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ሶዶ ቅ/ጽ/ቤት ግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር በመምጣት 100 ብር ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
- የባለቤትነት ይዞታ ማረጋገጫ ሰነድ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፍኬት፣ ታክስ ክሊራን ሰርተፍኬት / ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ሶዶ ቅ/ጽ/ቤት ስም የተዘጋጀ፣ በቅድመ ሁኔታ ያልተገደበ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የባንክ ጋራንቲ ወይም CPO ብር 5,000 ከመጫረቻ ሠነድ ጋር ተያይዞ መቅረብ ይኖርበታል::
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት የአገልግሎት ግዥ ለተጫራቾች በሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ክፍል 6 ላይ ከተመለከተው የቴክኒክ ፍላጎት ጋር መጣጣም ይኖርበታል፡፡::
- ሠነዳቸውን አንድ ኦሪጅናልና አንድ ኮፒ ለየብቻው በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ እስከ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው በዚሁ ቀን 8፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በሚገኙበት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት በአዲሱ በግዥና ፋይናንስ ንብረት አስተዳደር ቢሮ ይከፈታል፡፡ ሆኖም ይህ ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም በበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ይሆናል፡፡
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ስልክ ቁጥር 0962331133/0465512346/0913929850
የኢትዮጵያ ስታትስቲክስ አገልግሎት ሶዶ ቅ/ፅ/ቤት
