በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጎጥ መሪዎች አገልግሎት የሚውል ዩኒፎርም፣ ቦርሣ፣ ጃንጥላ ዕቃዎችን በጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
SIDAMA NATIONAL REGIONAL STATE HEALTH BUREAU (የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ)
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ጤና ቢሮ በ2017 በጀት ዓመት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን የጎጥ መሪዎች አገልግሎት የሚውል ዩኒፎርም፣ ቦርሣ፣ ጃንጥላ ዕቃዎችን በጨረታ ማስታወቂያ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚሁ መሠረት፤
- ዩኒፎርም አልባሳት
- ቦርሳ
- ጃንጥላ
- የንግድ ፍቃዳቸው የምዝገባ ሠርተፍኬታቸውን ለ2017 ዓ/ም ያሳደሱ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፣
- ተጨማሪ እሴት ታከስ የተመዘገቡ ጨረታውን በክልል ሲዳማ ጤና ቢሮ በማቅረብ ለግዥ የተዘጋጀውን ሰነድ የማይመለስ ብር 150 /አንድ መቶ ሃምሳ ብር/ በመክፈል ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለ15 ተከታታይ ቀናት ዘወትር በሥራ ሰዓት ከቢሮ ቁጥር 27 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ከሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ CPO 2% የጨረታ ዋስትና በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ሲፒኦ ማስያዝ የሚችል፤ ሆኖም በሂሳብ ስሌት ምርመራ የተገኘው የጨረታ ዋስትና ከቀረበው ዋጋ በታች ሆኖ ከተገኘ ከጨረታ ውጪ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሠነዳቸውን ቴክኒካልና ፋይናንሻል ለእያንዳንቸው አንድ ኦርጂናል እና ሁለት ኮፒ ለየብቻው ኤንቨሎፕ ፖስታ ማቅረብ አለባቸው፣ በመሆኑም ከዚህ በላይ ከተገለጸው ውጪ የሚያቀርቡ ከውድድር ውጪ ያስደርጋል፡፡
- ተጫራች የቀረቡ ዕቃዎች የከለሩ ምርጫ መ/ቤቱ በሚመርጠው መሠረት ይሆናል፤
- ተጫራቾች እያንዳንዱ በሚያቀርቡት ፖስታዎች ላይ የድርጅቱ ስምና ማህተም በግልፅ መቀመጥ አለበት፤
- ጨረታው በ16ኛው የሥራ ቀን ከ4፡00 ሰዓት እስከ 6፡00 ሰዓት ድረስ የግ/ፋይ/ንብ/አስ/ዳይሬክቶሬት ግዥ ክፍል በተዘጋጀው ጨረታ ሣጥን በማስገባት በተጠቀሰው ሰዓት ይታሸጋል፣ በዚሁ ዕለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው) በተገኙበት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 0462126783 ይጠይቁን
የሲ/ብ/ክ/መንግስት ጤና ቢሮ
