የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲ/ግ/ስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን ለስፖርት ምክር ቤት የተለያዩ የስፖርት ግዥዎችን የዕቃ ግዥዎችን በ 2 ምድብ ከፍሎ በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲ/ግ/ስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
ቁጥር 004/2017
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲ/ግ/ስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት የመንግሥት ግዥ ቡድን ለስፖርት ምክር ቤት የተለያዩ የስፖርት ግዥዎችን የዕቃ ግዥዎችን በ 2 ምድብ ከፍሎ በግልጽ ጨረታ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት፡-
ሎት 1 የስፖርት ትጥቅ ሎት 2 ጅምናዚየም ግብዓት
ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉበትንና አግባብነት ያለው የታደሰ የንግድ ፈቃድ እና የንግድ ምዝገባ፣ ቲን ሰርተፊኬት ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር ወይም ከፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ በዕቃ አቅራቢነት የተመዘገቡበትን የምስክር ወረቀት እና የቫት ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ መረጃ ክሊራንስ ከጨረታው ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 300 /ሶስት መቶ ብር/ በመክፈል ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 10 የሥራ ቀናት ውስጥ ከላይ የተጠቀሱትን መረጃዎች ዋናውንና ኮፒውን በማቅረብ ዘወትር በሥራ ሰዓት መውሰድ ይችላሉ።
- የጨረታ ሰነዱ በኤንቨሎፕ ታሽጎ ለዚሁ ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ፋይናንሻል ዋናውንና ኮፒውን ለየብቻ እንዲሁም ቴክኒካል ዋናውና ኮፒው ለየብቻ በኤንቨሎፕ ታሽጎ በኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲ/ግ/ስ/ፑል የመንግሥት ግዥ ቡድን 3ኛ ፎቅ መግባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሠዓት ሰነዱ ተመላሽ ተደርጎ በዚህ ቀን ጠዋት በ4፡30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በጋዜጣው ላይ በተገለጹት የጨረታ ዓይነቶች በሙሉ ወይም በከፊል መጫረት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሙሉ ስማቸውን፣ አድራሻቸውንና ፊርማቸውን የድርጅቱን ማህተም በእያንዳንዱ ሰነድ ገጽ ላይ በመፈረም ማቅረብና ማረጋገጥ አለባቸወ::
- የጨረታ ማስከበሪያ ሎት 1 ያሉት 10,000 ብር ሎት 2 30,000 ብር በባንክ በተረጋገጠ CPO ወይም ጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዝ ከሆኑ ከአደራጃቸው አካል የድጋፍ ደብዳቤ በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ዲ/ግ/ስ ፑል የመንግሥት ግዥ ቡድን ስም ተሠርቶ መቅረብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች በሚወዳደሩበት ጨረታ የጨረታ ዓይነቶች ውስጥ የተዘረዘሩትን ያንዱን ዋጋ እና የጠቅላላውን ዋጋ በግልጽ ከጽ/ቤት ገዝተው በወሰዱት ሰነድ ላይ ማስፈር ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ሎት 1 በተገለፁት የጨረታ ዓይነቶች ናሙና የማቅረብ ግዴታ ያለባቸው ሲሆን ሌሎቹ በጨረታ ሰነዱ በተገለፀው ስፔስፊኬሽን መሰረት ዋጋ መሙላት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- ኮ/ቀራኒዮ ክ/ከተማ ወረዳ 06 የሚገኘው የክፍለ ከተማው ህንፃ 3ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 301/
ስልክ ቁጥር፡- 011834 77 32
የኮ/ቀ/ክ/ከተማ አስተዳደር ዲ/ግ/ስ ፑል አስተዳደርና ፋይናንስ ጽ/ቤት
