Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉራጌ ዞን ምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ጉራጌ ዞን : ደቡብ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0113430173
  • Website
  • Deadline26 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-26 00:00:00
  • Categories Electrical And Electromechanical

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት አንድ የመንገድ ዳር መብራት አምፖል፣ ሎት ሁለት ሞንታርቦ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በጉራጌ ዞን ምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 0001

 

በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግሥት በጉራጌ ዞን የምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በስሩ ለሚገኙ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውሉ ሎት አንድ የመንገድ ዳር መብራት አምፖል፣ ሎት ሁለት ሞንታርቦ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።

በመሆኑም:-

              1. የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት፣ በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፍቃድ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር፤ የተ. እ.ታ ተመዝጋቢ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት እና በጨረታ መሳተፍ እንዲችሉ የተሰጠ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
              2. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በሲፒኦ ብቻ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 20000 (ሃያ ሺ ብር) በም/አ/ወ/ፋይናንስ ጽ/ቤት ስም ማሠራት ይጠበቅባቸዋል፡፡
              3. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን በም/አ/ወ/ገቢዎች ጽ/ቤት የማይመለስ 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል ከምሁርና እክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ግዢ ቢሮ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት እስከ ቀኑ 5፡00 ድረስ መግዛት ይችላሉ፡፡
              4. ተጫራቾች የእያንዳንዱ ሎት ኦርጅናልና ሁለት ቅጂ ሰነዶችን በመለየት በታሸገ ፖስታ በማድረግ ይህ ጨረታ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ አስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ማቆያ ሳጥን ማስገባት ይጠበቅባቸዋል የጨረታው ማስከበሪያው በኦርጅናል ዶክመንት ውስጥ መሆን ይኖርበታል፡፡
              5. የጨረታ አሸናፊው ዕቃዎቹን እስከ ቢሮአችን የሚያጓጉዝ ወጪ በራሱ ይሸፍናል፡፡
              6. ጨረታው በአስራ አምስተኛው ቀን ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ታሽጎ 8:30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታው እንዳይከፈት አያደርግም።
              7. ጽ/ቤቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 0113430173/0113430614 ይደውሉ

 

በጉራጌ ዞን ምሁርና አክሊል ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለነገዋ የሴቶች ተሃድሶና ክህሎት ማበልጸጊያ ማዕከል በ2019 በጀት ዓመት በ3 ሎት የተከፈሉ ግዥዎችን ለሁለተኛ ዙር በግልፅ ጨ...

READ MORE
MSF Belgium Ethiopia Mission Tender for Supply of Various Types of Stabilizers (Tender Ref. ET121 &...

READ MORE