Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ
  • Address Bahirdar Ethiopia, Bahir Dar, Ethiopia, Phone: 0582222270
  • Website
  • Deadline24 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-24 00:00:00
  • Categories Sport Materials And Sportswear

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለ2017 ዓ.ም ለስፖርት አገልግሎት የሚውሉ የስፖርት ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ


 

ግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 04

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ለ2017 ዓ.ም ለስፖርት አገልግሎት የሚውሉ የስፖርት ቁሳቁሶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል። ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የምታሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን ይጋብዛል።

  1. በዘርፋ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣
  2. የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ ፣
  3. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN) ያላቸው ፣
  4. የግዥው መጠን ከብር 200,000.00 (ሁለት መቶ ሺህ ብር) በላይ ከሆነ የተጨማሪ ዕሴት ታክስ (VAT) ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
  5. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተቁ 1- 4 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶች ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው:
  6. የሚገዙ ዕቃዎች አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይቻላል ፡፡
  7. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብር በመክፈል ከገንዘብ ያዥ ክፍል ቢሮ ቁጥር 32 ማግኘት ይችላሉ፡፡
  8. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ወይም የዕቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1% በባንክ በተረጋገጠ ክፍያ ትዕዛዝ (ሲፒኦ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ አለባቸው::
  9. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆነ በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በግዥ ፋ/ን/አ/ዳይሬከቶሬት ቢሮ ቁጥር 05 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ጋዜጣው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀናት ከጠዋቱ 3:00 ድረስ በሳጥኑ ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ 3፡05 ሳጥኑ ይታሸጋል፡፡
  10. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ቁጥር 05 በ16ኛው ቀን በ3፡30 ይከፈታል፡፡ ጨረታው በሚከፈትበት ቀን የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል፡፡
  11. ጨረታው የሚገመገመው በሚቀርበው የተናጠል ዋጋ ነው፡፡
  12. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 05 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 0582222270/0582262177 በመደወል ማግኘት ይችላሉ ፡፡

 

በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የወጣቶችና ስፖርት ቢሮ

 

Save Tender