ድርጅታችን ስኬት ኢንተርናሽናል አ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በማወዳደር ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሶስት አመት ተከታታይ አመታት የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል::
ስኬት ኢንተርናሽናል አክሲዮን ማህበር
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
ድርጅታችን ስኬት ኢንተርናሽናል አ/ማህበር ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በማወዳደር ከ2017 በጀት ዓመት ጀምሮ ለሶስት አመት ተከታታይ አመታት የማህበሩን ሂሳብ በውጭ ኦዲተር ማስመርመር ይፈልጋል::
ስለሆነም-
1ኛ/ የኦዲት ሥራ ለመስራት የሚያስችል የሙያ ፈቃድና የሙያ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፣
2ኛ/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለውና ማቅረብ የሚችል፤
3ኛ/ የግብር ከፋይ እና ተጨማሪ እሴት ታክስ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችል፤
4ኛ/ ከዚህ ቀደም አክሲዮን ማህበራትን ኦዲት ያደረገ ስለመሆኑ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል፤
ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውንም የውጭ ኦዲተር ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 21 ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ የቴክኒክ እና የፋይናንሻል መወዳደሪያ ሰነዶቻችሁን በታሸገ ኤንቮሎፕ በማድረግ በአክሲዮን ማህበሩ 7ኛ ወለል ቢሮ ቁጥር 701 በአካል በመቅረብ መመዝገብ ትችላላችሁ፡፤
አድራሻ፡- መርካቶ ራጉኤል ቤተክርስቲያን ፊት ለፊት በሚገኘው ስኬት ኢንተርናሽናል አ/ማህበር
ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 011 2 73 49 04 መደወል ይቻላል፣
ማሳሰቢያ፡- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ስታቀርቡ IFRS እና GAAP ተብሎ በተናጠል ማቅረብ ይጠበቅባችኋል::
ስኬት ኢንተርናሽናል አክሲዮን ማህበር
