የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዋልጋ ማዘጋጃ ቤት የገረጋንቲ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር፡- 07/2017
የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ለዋልጋ ማዘጋጃ ቤት የገረጋንቲ ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው መሳተፍ የምትፈልጉ ተጫራቾች የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት መውሰድ ትችላላችሁ።
- የዘመኑ የታደሰ የንግድ ህጋዊ ፈቃድ፤ ተጨማሪ እሴት ታከስ ወረቀት፤ የግብርከፋይ መለያ ቁጥር፤ የምዝገባ ሰርተፊኬት የምስክር ወረቀ፤ የግብዓት አቅራቢነት የንግድ ህጋዊ ፈቃድ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /10,000/ አስራ ሺህ ብር ከባንክ በተረጋገጠ /ሲፕኦ/ በማያያዝ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ከጨረታ ሰነዱ ጋር አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- የሚጫረቱበትን ዋጋ በመግለጽ የጨረታውን ሰነድ በታሸገ ኤንቨሎፕና አስፈላጊውን ማስረጃ ጋር በማያያዝ ዶክመንቱን ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው የሚከፈተው ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆይና በ16ኛው ቀን በ8፡00 ሰዓት ታሽጎ በ8፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
በተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር፡- 011-3-30-20-79 ደውለው ማነጋገር ይችላሉ፡፡
ማሳሰቢያ-
1ኛ. ጨረታው የሚከፈትበት ቀን በዓል ወይም ቅዳሜና እሁድ የሆነ ከሆነ ወደሚቀጥለው የስራ ቀን ይዘዋወራል፡፡
በጉራጌ ዞን የአበሽጌ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
