በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት የሆቴሎች አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር:- MOR JBO-002/2017
በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለ2017 በጀት አመት የሆቴሎች አገልግሎት ግዥ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ከዚህ በታች የተገለፁትን መስፈርቶችን የሚያሟሉ ተጫራቾች ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በሆቴል ዘርፍ የተሰማሩበት በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፤ የተ.እ.ታ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ በባህልና ቱሪዝም ሚኒስቴር ወይም ከሚመለከተው አካል የተሰጠ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣ ለአሶሳ፣ ጋምቤላ፣ ሚዛን እና ነቀምት ታክስ ማዕከል ሆኖ የኮከብ ደረጃ መስፈርት ግዴታ አይደለም፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ቢድ ቦንድ) ጠቅላላ የሞላችሁትን የአገልግሎት ዋጋ 0.5% እስከ 2% በማስላት በባንክ ክፍያ ማስያዣ (CPO) ወይም በጥሬ ገንዘብ በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅ/ጽ/ቤት ስም ማስያዝ የሚችሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) የሥራ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ ከጠዋቱ 2፡00-6:00 እና ከሰዓት 7:00-11:00 ሰዓት እንዲሁም ቅዳሜ ጠዋት ከ2፡00-6:00 ሰዓት በገቢዎች ሚኒስቴር ጅማ ቅ/ጽ/ቤት መርካቶ አዋሽ ባንክ ህንፃ 4ኛ ፎቅ ድረስ በመምጣት መግዛት ይችላሉ፡፡
- የአገልግሎት ዝርዝር መግለጫ ከጨረታ ሰነዱ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ በጥንቃቄ በመሙላት በእያንዳንዱ ገጽ ላይ ፊርማና የድርጅቱ ማህተም በመምታት በታሸገ ኤንቨሎፕ ቴክኒካሉን እና ፋይናንሽያሉን ዋናው እና ኮፒው ለየብቻ በኤንቨሎፕ ወይም ካኪ ፖስታ በማሸግ በቅ/ጽ/ቤት በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ማስገባት የሚችሉ፡፡
- ጨረታው የሚዘጋበትና የሚከፈትበት ሰዓት ከጨረታ ሰነድ ላይ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የጨረታ ሰነድ መቀየር፣ ማሻሻል ወይም ከጨረታው ራስን ማግለል አይቻልም፡፡
- የተሰረዘና የተደለዘ፣ የተፋፋቀ እንዲሁም በግልጽ የማይነበብ የጨረታ ዋጋ ተቀባይነት አይኖረውም።
- መሥሪያ ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ በህግ የተጠበቀ ነው::
- ለተጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥር 047-1-11-56-00/ 047-2-11-04-43 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ።
በገቢዎች ሚኒስቴር የጅማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት
