የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እገልግሎት የደሴ ሪጅን በስሩ ለሚገኙት ለ9 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት 3ኪሎ ዋት አል ኢን ዋን ከኤሌክትሪክ እና ከፀሀይ ብርሀን (ሀይበርድ ቴክኖሎጂ) ቻርጅ የሚያደርግ ኢንቨርተር ባትሪ መግዛት ይፈልጋል፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደሴ ሪጅን
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: EEU/D/R/011/2017
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ እገልግሎት የደሴ ሪጅን በስሩ ለሚገኙት ለ9 አገልግሎት መስጫ ማዕከላት 3ኪሎ ዋት አል ኢን ዋን ከኤሌክትሪክ እና ከፀሀይ ብርሀን (ሀይበርድ ቴክኖሎጂ) ቻርጅ የሚያደርግ ኢንቨርተር ባትሪ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም ዕቃውን ማቅረብ መግጠም እና ስልጠና መስጠት የሚፈልግ ድርጅት በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
በዚህ ጨረታ መሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች፡-
- በዘርፉ የተሰማራ የዘመኑን ግብር የተከፈለበት የታደሰ ንግድ ፍቃድ፣ በፌዴራል መንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ያልታገደ ፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያለው የታደሰ የታክስ ክሊራንስ ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችል
- ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫ የያዘውን የጨረታ ሠነድ ለመግዛት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ገንዘብ ብር 350.00 (ሶስት መቶ ሃምሳ ብር) በኢ/ኤ/አገ/ ደሴ ሪጅን ጽ/ቤት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000151866248 በማስገባትና የባንክ ደረሰኙን ከታች በሚገኘው አድራሻ በማቅረብ መግዛት ይችላል፡፡ ደሴ ከተማ መናፈሻ ክፍል ከተማ ፀዳይ ባንክ በሚገኘው የድርጅቱ ቢሮ የኢ/ኤ/አገ/ ደሴ ሪጅን ግዥ፣ ሎጀስቲክስ፣ ንብረት እና ፋሲሊቲ ቢሮ ቁጥር 016
- ተጫራቶች ብር 50,000.00(ሀምሳ ሺህ ብር ከ00/100) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ (CPO) ወይም በሁኔታዎች ላይ ያልተመረኮዘ የባንክ ጋራንቲ (Bid Bond) ማስያዝ የሚችል ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
- ተጫራቾች ከዚህ በላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎች በማሟላት የጨረታ ሰነዳቸውን ጨረታው ከወጣበት መጋቢት 30 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ በስራ ሰዓት እስከ ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለዚህ ጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ባይገኙም ሚያዝያ 20 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 9፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት በደሴ ሪጅን የሰፕላይቼይን ማኔጅመንት ንብረት እና ጠቅላላ አገልግሎት ቢሮ ፀዳይ ባንክ ህንፃ ምድር ቤት ቢሮ ቁጥር 16 ይከፈታል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጫራቾች መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥር 0935815152 መጠየቅ ይችላሉ፡፡
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ደሴ ሪጅን
