በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለማሻ ወረዳ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ /ሕ/ክ/መንግስት ሸካ ዞን ማሻ ከተማ ፋይናንስ ፅ/ቤት
ለመጀመሪያ ጊዜ የወጣ የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለማሻ ወረዳ ሴ/ር መ/ቤቶች አገልግሎት የሚውል የተለያዩ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚሁ መሰረት
ሎት 1ኛ የተለያዩ ኤሌክትሮኒክሰ ዕቃዎች
ሎት 2ኛ የደንብ ልብስ
ሎት 3ኛ ብርድልብስና ፍራሽ
ሎት 4ኛ የመኪና ጎማ
ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ከአሸናፊ ድርጅት ከላይ የተዘረዘሩትን ዕቃዎች ለመግዛት ይፈልጋል በዚሁ መሰረት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች ማሟላት የሚችሉትን ተጫራቾችን ይጋብዛል
- በመስኩ ህጋዊ የንግድ ስራ ፍቃድ ያለውና የ2017 በጀት ዓመት የታደስ የንግድ ስራ ፍቃድ ማቅረብ የሚችል በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ ስለመመዝገባቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችልና ተጨማሪ የእሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ አለበት ::
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ለእያንዳንዳቸው ብር 5000 /አምስት ሺህ ብር/ ከኢት/ያ ንግድ በባንክ የተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለባቸው::
- ተጫራቾች የጨረታ ማወዳደሪያ ሰነድ ለእያንዳንዱ የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ) ብር ከማሽ ወረዳ /ባ/ሥ/ቅ/ጽ/ቤት በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ከማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 2 (ሁለት) መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታውን ሰነድ በሰም በታሸገ ፖስታ በማድረግ ኦርጅናልና ኮፒ በመለየት ፊርማና የድርጅቱን ማህተም ከማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ጊዜ ጀምሮ ለ 15 ተከታታይ የስራ ቀናት ማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ለዚህ ጨረታ አገልግሎት በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፤
- ጨረታው በ16ኛ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት (አራት ሰዓት) ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወከሎቻቸው በተገኘበት ይከፈታል በ16ኛው ቀን የመንግስት ሥራ ሰዓት ካልሆነ በሚቀጥለው በመንግስት የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታ አሸናፊ የሆነው አቅራቢ ዕቃዎቹን አጓጉዞ በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋ/ኢ/ል/ጽ/ቤት ማቅረብ አለበት።
- ተጫራች የውል ማስከበሪያ ከጠቅላላ ዋጋ 10% ለማስያዝ ፍቃደኛ መሆን አለበት።
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥሮች- 0475580293 ወይም 0912789043 ወይም 0925270431 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል መንግስት በሸካ ዞን በማሻ ወረዳ ፋይናንስ ኢ/ል/ጽ/ቤት
