የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸገር ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ስር ላሉት የጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መሳሪያዎችን እና ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚውል የኃይል ማመንጫ ሶላር ሲስተም /Solar Hybrid/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጨረታ መመሪያ በመከተል ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ለሸገር ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት ስር ላሉት የጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ የህክምና መሳሪያዎችን እና ኤሌክትሪክ ለማመንጨት የሚውል የኃይል ማመንጫ ሶላር ሲስተም /Solar Hybrid/ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ስለሚፈልግ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለፀውን የጨረታ መመሪያ በመከተል ጨረታውን እንዲካፈሉ ተጋብዘዋል፡፡
በዚሁ መሠረት ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት ቅዳሜን ጨምረው ከሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት የማይመለስ ብር 500.00 (አምስት መቶ ብር) በሲንቄ ባንክ በተከፈተው ሂሣብ ቁጥር 1064540111215 ገቢ በማድረግ ዲፖዚት ስሊፑን /Deposit slip/ ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንፃ አንደኛ ፎቅ የፋይናንስ አስተዳደር ዳይሬክተር ክፍል በማቅረብ እና ገቢ ደረሰኝ በማስቆረጥ የጨረታ ሰነዱን 3ኛ ፎቅ ከሸገር ከተማ አስተዳደር ጤና ጽ/ቤት መዝገብ ቤት ክፍል መውሰድ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
የተጫራቾች ግዴታዎች
- በዘርፉ ህጋዊ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር የከፈሉ ለዚሁም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው እና ቫት ማስረጃውን ማቅረብ የሚችሉ፤
- በፌዴራል ገ/ሚኒስቴር ወይም በኦሮሚያ ገ/ቢሮ ወይም ከሚመለከተው መ/ቤት አቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተመሰከረ 100,000.00 ብር CPO (ሲፒኦ) ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ውል ሲፈርሙ የውል ማስከበሪያ (ዋስትና 10%) ማስያዝ ይኖርባቸዋል::
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነዱ ላይ ብቻ በመሙላት በኦርጅናል እና በኮፒ በመለየት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የመንግስት የሥራ ቀናት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት ህንጻ ግዥ ንብረት አወጋገድ እና አስተዳደር ጠቅላላ አገልግሎት ዳይሬክተር 2ኛ ፎቅ ለዚሁ በተዘጋጀው ሣጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ጨረታው በ16ኛው ቀን ጠዋት 4፡00 ተዘግቶ በዕለቱ 4:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት አዳራሽ ይከፈታል፡፡ እለቱ የመንግሥት የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
- ጽ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለጨማሪ መረጃ በስልክ ቁጥሮች:- 0114-70-93-00/0912023101 በመደወል መረዳት ይችላሉ፡፡
አድራሻ፡- ሳሪስ በአልትሜት ሞተርስ ገባ ብሎ የቀድሞው የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ ቅጥር ግቢ ውስጥ
የሸገር ከተማ አስተዳደር ገንዘብ ጽ/ቤት
ፊንፊኔ
