የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ ም በቁጥር ገ/ኢ/153/68 ከገንዘብ ሚኒስቴር ለድርጅታችን በቀጥታ በፃፈው ደብዳቤ በየተቋማቱ የሚገኙ የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ስክራፕ የተደረጉ ተሽከርካሪዎች፤ ማሽነሪዎች እና አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን በኪሎ ግራም ዋጋ ለብረታ ብረት አቅላጭ በውድድር እንዲሸጥ በፈቀደው መሰረት ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲከስ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ኮንቴይነሮችን፤ ገጀራዎችን፤ በስከራፕ መልከ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎችን፤ ማሸነሪዎችን እና አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን እና የመሳሰሉትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የገንዘብ ሚኒስቴር ለብረት አቅላጭ በኪሎ ግራም የገቢያ መነሻ ዋጋ ብሎ በወሰነው መሰረት በብረታ ብረት አቅላጭነት የተሰማሩትን በገቢያ በማወዳደር ለመሸጥ ይህ የግልፅ ጨረታ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2007ዓ.ም ወቷል።
Ethiopian Shipping and Logistics (የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ)
የብረታ ብረት የግልፅ ጨረታ ሽያጭ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር DS 01/2017
ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ ም በቁጥር ገ/ኢ/153/68 ከገንዘብ ሚኒስቴር ለድርጅታችን በቀጥታ በፃፈው ደብዳቤ በየተቋማቱ የሚገኙ የቁርጥራጭ ብረታ ብረቶች፣ ስክራፕ የተደረጉ ተሽከርካሪዎች፤ ማሽነሪዎች እና አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን በኪሎ ግራም ዋጋ ለብረታ ብረት አቅላጭ በውድድር እንዲሸጥ በፈቀደው መሰረት ድርጅታችን የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲከስ ቁርጥራጭ ብረታ ብረቶችን፣ ጉዳት የደረሰባቸው ኮንቴይነሮችን፤ ገጀራዎችን፤ በስከራፕ መልከ የሚሸጡ ተሽከርካሪዎችን፤ ማሸነሪዎችን እና አገልግሎት ሰጥተው ወደ መጋዘን የተመለሱ የተሸከርካሪ መለዋወጫዎችን እና የመሳሰሉትን ንብረቶች ባሉበት ሁኔታ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ የገንዘብ ሚኒስቴር ለብረት አቅላጭ በኪሎ ግራም የገቢያ መነሻ ዋጋ ብሎ በወሰነው መሰረት በብረታ ብረት አቅላጭነት የተሰማሩትን በገቢያ በማወዳደር ለመሸጥ ይህ የግልፅ ጨረታ ማስታውቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ዛሬ መጋቢት 24 ቀን 2007ዓ.ም ወቷል።
በመሆኑም በብረታ ብረት እቅላጭነት ዘርፍ ተሰማርታችሁ በማዕድን ሚኒስቴር እውቅና ያላችሁ እና የገንዘብ ሚኒስቴር ባስተላለፈው መመሪያ መሰረት በግልፅ ጨረታው ለመሳተፍ ፍቃደኛ የሆነ በድርጅታችን የተዘጋጀውን የጨረታ ሰነድ ይህ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 5 ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 1000.00 /አንድ ሺህ/ በመክፈል ለገሃር በሚገኘው የድርጅቱ ዋና መሥሪያ ቤት ህንፃ ሶስተኛ ፎቅ ፋይናንስ ቢሮ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
የጨረታውን ሰነድ ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 5ኛው የሥራ ቀን እና የጨረታ ሳጥኑ እስከሚታሸግበት 6ኛው ቀን እስከ 8፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ህንፃ 6ኛ ፎቅ በመቅረብ ለዚሁ ተግባር በተዘጋጀው ሳጥን የጨረታ ሰነዱን በፖስታ ውስጥ በማሸግ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል። ጨረታው በዚሁ ዕለት ከሠዓት 8፡00 ተዘግቶ በዚሁ እለት 8፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው በግልዕ ይከፈታል። ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በራሳቸው ፈቃድ ካልተገኙ ተቋሙ ጨረታውን ከመከፈት አይታገድም።
ድርጅቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
ስለ ጨረታው ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር 0115549257/095144204 ማብራሪያ ማግኘት ይቻላል።
የኢትዮጵያ የባህር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ
