Tender Detail

Tender Details

  • Company በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ጎጃም : አማራ ክልል ፡ ኢትዯጵያ, Phone: 09 13 27 18 23
  • Website
  • Deadline17 Apr 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-17 00:00:00
  • Categories Food And Beverage , Steel, Metals And Aluminium , Vehicle Battery

በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የመኪና መለዋወጫ ዕቃ /ለ2ኛ ጊዜ/፤ ሎት 2. የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር፣ ሎት 3. የምግብ ምርቶች/በኮንትራት ውል አቅርቦት/፣ ሎት 4. የእህል ምርት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በምሥራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት


 

 ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 03

 

በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት በወረዳው ውስጥ ለሚገኙ ባለበጀት መ/ቤቶች ለተለያዩ አገልግሎት የሚውሉ ሎት 1. የመኪና መለዋወጫ ዕቃ /ለ2ኛ ጊዜ/፤ ሎት 2. የቤት ክዳን ቆርቆሮና ሚስማር፣ ሎት 3. የምግብ ምርቶች/በኮንትራት ውል አቅርቦት/፣ ሎት 4. የእህል ምርት ውጤቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር የሚችሉ መሆኑን ይጋብዛል፡፡

  1. በዘመኑ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /ቲን ነምበር/ ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤

  2. የግዥ መጠኑ ከብር 200,000.00 /ሁለት መቶ ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ/ የቫት ከፋይነት /የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡

  3. ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-2 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡

  4. የሚገዛውን እቃ ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከመጫረቻ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡

  5. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ለእያንዳንዱ ሎት ብር 100.00 /አንድ መቶ ብር/ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአነደድ ወረዳ የወረዳ በጀት ማስፈጸሚያ አካውንት ቁጥር 1000091375048 በማስገባት ደረሰኙን በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡

  6. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ቢድ ቦንድ ለሚወዳደሩበት ጥቅል ዋጋ ለሎት -1 ብር 10,000.00 /አስር ሺህ ብር/፣ ለሎት 2 ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 3 ብር 3,000.00 /ሶስት ሺህ ብር/፣ ለሎት 4. ብር 700.00 /ሰባት መቶ ብር/ በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትእዛዝ ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና አሊያም በጥሬ ገንዘብ ከሆነ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አነደድ ወረዳ የወረዳ በጀት ማስፈጸሚያ አካውንት ቁጥር 1000091375048 ላይ ገቢ አድርገው ሰነዱን ማቅረብ አለባቸው፡፡ 

  7. ማንኛውም ተጫራች ሃሳቡን በአንድ ወይም በሁለት ቅጅዎች ዋናና ቅጅ በማለት ኦርጅናሉን ለብቻ ኮፒውን ለብቻ በታሸገ ፖስታ በማድረግ ስሙን፤ ፊርማውንና ማህተሙን በማሳረፍ አነደድ ወረዳ ሲቪል ሰርቪስ ግቢ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ዘወትር በስራ ሰዓት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀንና እስከ 16ኛው ቀን 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት አለባቸው::

  8. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 3፡30 ታሽጎ በ4፡00 ሰዓት ላይ ይከፈታል፡፡ እለቱ የስራ ቀን ካልሆነም በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይከፈታል፡፡ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በጨረታ መክፈቻ ሰዓቱ ባይገኙም መ/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብት አለው:: በጨረታ መክፈቻ ቀንና ሰዓት ያልተገኙ ተወዳዳሪዎች በተላለፈው ውሳኔ ተገዥ ይሆናሉ፡፡

  9. አሸናፊው አካል ያሸነፈባቸውን እቃዎች ጠቅላላ ወጪውን በመሸፈን አነደድ ወረዳ ግብርና ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፤ ለሁሉም ሎቶች ለውል መያዣ የሚፈለጉ ወጪዎችን አሸናፊው አካል የሚሸፍን ይሆናል፡፡

  10. ግዥ ፈጻሚው አካል ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ሲሆን በጨረታው መሰረዝ ምክንያት ለወጣው ወጭ መ/ቤታችን ተጠያቂ አይሆንም።

  11. ውድድሩ የሎት 1 በነጠላ ዋጋ፣ የሎት 2 እና 3 በጥቅል ዋጋ ስለሚታይ ተጫራቾች በአንድ ሎት ያሉትን ዝርዝር እቃዎች ሁሉንም ዋጋ መሙላት ያለባቸው ሲሆን ግዥ ፈጻሚው አካል ካወጣው ስፔስፊኬሽን ውጭ በራሱ ስፔስፊኬሽን የሞላ ተወዳዳሪ ከውድድር ውጭ ይሆናል፡፡

  12. በውድድሩ አሸናፊ የሆኑ ተወዳዳሪዎች ሙያ የሚጠይቁ እቃዎችን በሚመለከተው ባለሙያ የሚያረጋግጥ ይሆናል፡፡

  13. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልግ ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለገ አነ/ወ/ ሲ/ሰ/ጽ/ቤት ውስጥ በሚገኘው ገንዘብ ጽ/ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ቁጥር 01 በአካል ወይም በስልክ ቁጥራችን 09 13 27 18 23/09 46 08 84 03 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

በአብክመ በምስራቅ ጎጃም ዞን የአነደድ ወረዳ ገንዘብ ጽ/ቤት

  

Save Tender