በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለሐኪም ግዛው ሆስፒታል ለህክምና ባለሙያዎችና ለታካሚዎች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ግዥ ስራ አስፈፃሚ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር :- DBU/AWHSC/09/2017
በደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ለሐኪም ግዛው ሆስፒታል ለህክምና ባለሙያዎችና ለታካሚዎች አገልግሎት የሚውል የደንብ ልብስ በዘርፉ ከተሰማሩ አቅራቢዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በጨረታው ለመሳተፍ ፡-
-
ተጫራቾች ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ: የንግድ ምዝገባ ወረቀት፤ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር፣ በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገጽ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡበትን የተመዘገቡበትን ወረቀትና ወረቀትና የዘመኑን ግብር መክፈላቸውን ከግብር ሰብሳቢው ባለስልጣን የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው::
-
ተጫራቾች ለሚያቀርቡት አጠቃላይ ዋጋ ለ90 ቀናት ፀንቶ የሚቆይ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ከታወቀ ባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ ወይም የባንክ ጋራንት ብር 100,000 (አንድ መቶ ሺህ ብር) አሰርተው ከዋናው የዋጋ ሰነድ ጋር አያይዘው ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታውን ዝርዝር የሚያሳይ የጨረታ ሰነድና የተጫራቾች መመሪያ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ 300 (ሶስት መቶ ብር) ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርስቲ አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በየትኛውም ቅርንጫፍ በሂሳብ ቁጥር 1000655215054 ገቢ በማድረግና በካምፓሱ ፋይናንስ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር F1-03 ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ ቀኑ 10፡00 ሰዓት ድረስ ማህተም በማስደረግ ከግዥ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር G-01 ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ ዋናና ቅጅ (Original and copy) ለየብቻ በታሸገ ኤንቨሎፕ የጨረታ ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ብቻ በዩኒቨርስቲው የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ከግዥ ስራ አስፈጻሚ ቢሮ ቁጥር G-01 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ በ16ኛው ቀን በ4፡00 የጨረታው ሳጥን ታሽጎ ዋጋ የቀረቡ ናሙናዎች ግምገማ ከተከናወነ በኋላ በ8፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው፤ ከስነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና እና ከውስጥ ኦዲት ስራ አስፈጻሚ ባለሙያዎች እንዲሁም ጨረታውን መታዘብ የሚፈልግ ማንኛውም አካል በተገኙበት በካምፓሱ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ናሙና የተመረጠላቸው ተጫራቾች የዋጋ ሰነድ በግልጽ ይከፈታል፡፡ የመክፈቻ ዕለቱ በሳምንቱ የዕረፍት ቀናት የሚውል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ይከፈታል፡፡ /ትክክለኛውን የመክፈቻ ቀን በጨረታ ሰነዱ ላይ እንገልፃለን፡፡
-
ተጫራቾች በለላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
-
ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት በማጓጓዝ በአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ ንብረት ክፍል ገቢ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡
-
የጨረታው ውጤት ለአሸናፊና ለተሸናፊ ድርጅቶች በስልክና በደብዳቤ እንዲሁም በካምፓሱ የውስጥ ማስታወቂያ ሰሌዳ የምናሳወቅ ይሆናል፡፡ ተጫራቾች በሚወዳደሩት ሰነድ ላይ ዘወትር በስራ ሰዓት የሚሰሩ ስልኮችን ማስቀመጥ አለባቸው፡፡
-
ካምፓሱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡ ለበለጠ መረጃ በስልክ ቁጥር፡- 011-8-90-03-29 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
የአስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ካምፓስ የግዥ ስራ አስፈጻሚ
