የአርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ለ2017 የበጀት አመት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የዕቃና የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር አርዳይታ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ሥልጠና ኮሌጅ
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር አርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ግዥ 04/2017
የአርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ለ2017 የበጀት አመት የሚያስፈልጉትን የተለያዩ የዕቃና የአገልግሎት ግዥ ለመፈጸም ይፈልጋል።
በዚሁ መሰረት:-
-
ቴሌቪዥን፤ የራውተር ዕቃዎች እና አልጋ የሲፒኦ መጠን ብር 13,000.00 ነው::
-
የወተት ማሸጊያ ማሽን እና ሌሎች ዕቃዎች የሲፒኦ መጠን ብር 60,000.00 ነው::
-
ፋጉሎ፣ የምግብ ጨው እና አሞሌ ጨው የሲፒኦ መጠን ብር 30,000.00 ነው::
-
የላይብረሪ ፈርኒቸሮች የሲፒኦ መጠን ብር 15,000.00 ነው::
-
የግንባታ ዕቃዎች የሲፒኦ መጠን ብር 10,000.00 ነው::
-
ዘመናዊ የንብ ቀፎ እና ሌሎች እቃዎች የሲፒአ መጠን ብር 15,000.00 ነው::
-
የሰራተኞች የደንብ ልብስ የመስፋት ስራ የሲፒኦ መጠን ብር 25,000.00 ነው::
-
የሴሬሞኒ የቢሮ ውስጥ ጌጣ ጌጦች ቁሳቁሶች የሲፒኦ መጠን ብር 7000.00 ነው::
-
ለኃላፊ የሚሆን ወንበር፣ ጠረጴዛ፣ መጋረጃ እና ምንጣፍ የሲፒኦ መጠን ብር 10,000.00 ነው::
-
የተለያዩ የቀላል፣ የከባድ፣ የእርሻ ማሽነሪዎች መለዋወጫ ግዥ እና የጥገና ግዥ የሲፒኦ መጠን ብር 20,000.00 ነው::
-
ጂፒኤስ እና ሞተራይዝድ ኬሚካል መርጫ የሲፒኦ መጠን ብር 20,000.00 ነው::
በተራ ቁጥር 2፣ 3፣ 6 እና 11 ላይ የተዘረዘሩት ለኢንተርፕራይዝ ነው::
-
ተጫራቾች በዘመኑ የታደሰ ከሚያቀርቡት የዕቃ ግዥ ጋር ተያያዥነት ያለውን በዘመኑ የተገበረ ንግድ ፈቃድ ፣ በአቅራቢነት የተመዘገቡና የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይ ለመሆናቸው ማረጋገጫና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ማስረጃ /TIN/ ፎቶ ኮፒውን ማቅረብ አለባቸው:: ከዚህ በተጨማሪ ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የ2017 ዓ/ም የግብር ግዴታቸውን መወጣታቸውንና በጨረታ መካፈል መቻላቸውን ወቅታዊ የድጋፍ ደብዳቤ ከመልካም ስራ አፈጻጸም በቅርብ ግዜ የተሰጠ ማስረጃ አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
-
በጨረታ ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ዝርዝር መግለጫውን የያዘ የጨረታውን ሰነድ ይህ ማስታውቂያ በጋዜጣ ላይ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት አዲስ አበባ 22 ማዞሪያ ከጌት ፋም ሆቴል ገባ ብሎ በሚገኘው መንገድ አዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊት ለፊት ያለው አላጌ ግቢ ውስጥ በኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ አስተባባሪ ቢሮ እና በአርዳይታ ኮሌጅ የግዥ ቡድን መሪ ቢሮ በመቅረብ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ ከፍለው መውሰድ ይችላሉ፡፡
-
ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ሞልተው በታሸገ ኢንቨሎፕ የድርጅቱን ማህተም በማድረግ የጨረታ መመሪያውን በመከተል አዲስ አበባ በሚገኘው በኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን በኋላ እስከ 7/8/2017 ዓ/ም ከቀኑ 8:00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ የጨረታ ሰነዱን ማስገባት ይችላሉ፡፡ ተጫራቾች ስልክ ቁጥራቸውን በግልጽ በመሙላት የድርጅቱን ማህተምና በኃላፊ ፈርማ ማረጋገጥ ይኖርባቸዋል፡፡ የእቃዎቹ ማስረከቢያ ቦታ እና ልብስ የመስፋት ስራ ቦታ አርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ቅጥር ግቢ ውስጥ ዕቃ ግ/ቤት ነው::
-
ጨረታው በዕለቱ በ7/8/2017ዓ/ም ከቀኑ 8፡00 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ታሽጎ በዚሁ እለት ከቀኑ 8፡30 ሰዓት ላይ አዲስ አበባ ላይ ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ ጨረታው የሚዘጋውና የሚከፈተው በሚቀጥለው የስራ ቀን ይሆናል፡፡
-
ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
-
ለተጨማሪ ማብራሪያ አርዳይታ ግ/ቴ/ሙ/ስ/ኮሌጅ ስልክ ቁጥር 0224760021/16/ አዲስ አበባ 0116627150 ወይም ሞባይል 0913010114/ 0911707197/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ ፋክስ ቁጥር፡ 0227460025 ነው::
-
ማንኛውም ተጫራች ለሚወዳደርበት የዕቃም ሆነ የአገልግሎት ግዥ የሚያቀርበው ዋጋ ለ 60 (ስልሳ) ቀናት የጸና ይሆናል፡፡
በሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የአርዳይታ ግ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ
አርዳይታ
