አጋርፋ የግብርና ቴክኒከና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች እና አገልግሎቶች ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል።
Agarfa Agricultural Technical Vocational Educational & Training College (አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ)
የዕቃ ግዥ ጨረታ ማስታወቂያ የግዥ መሌያ ቁጥር 01/003/2017
አጋርፋ የግብርና ቴክኒከና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ የሚከተሉትን ዕቃዎች:-
-
የሠራተኞች የደንብ አልባሳት
-
የተለያዩ የእርሻ መሳሪያዎች (ማረሻ፣ መከስከሻና የኬሚካል መርጫ)፡
-
የተሽከርካሪ መለዋወጫ ዕቃዎችን፣ ጎማ እና የተሽከርካሪ ባትሪ፣
-
የእርሻ መሬት በኪራይ ማሽነሪ የማሳረስ ኪራይ የአገልግሎት ግዥ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል። ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ተጫራቾች ከዚህ በታች የተገለጹትን መመሪያዎችና ግዴታዎችን በማሟላት መወዳደር ይችላሉ፡፡
ጨረታው የሚከናወነው በግልጽ ጨረታ ሥነ-ስርዓትና ይህንኑ አስመልክቶ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግስት ባወጣው የመንግስት ግዥ አዋጅ መሠረት ብቁ ለሆኑ ሃገሮች ተጫራቾች ነው::
-
ተጫራቾች በጨረታው ለመሳተፍ
1.1. ከመስኩ ጋር አግባብነት ያለውና የአገልግሎት ጊዜው ያላለፈበት የታደሰ የሥራ / የንግድ ሥራ ፈቃድ፤
1.2. የግብር መክፈያ የምስክር ወረቀት /TIN/:
1.3. እንዲሁም እንደአስፈላጊነቱ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ የምዝገባ ምስክር ወረቀት፣
1.4. በመንግስት ኤሌክትሮኒክስ ግዥ ሥርዓት (e-Government procurement system) በአቅራቢነት የተመዘገቡ መሆን አለባቸው::
1.5. በመንግስት የግብር ህግ መሠረት ግብር የመክፈል ግዴታቸውን የተወጡና መንግስት በሚያወጣቸው ጨረታዎች ላይ መሳተፍ የሚችሉ መሆናቸውን የሚገልጽ ጊዜው ያላለፈበት የድጋፍ ደብዳቤ የምስክር ወረቀት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
1.6. ተጫራቾች የማጭበርበር ድርጊት ላለመፈፀም ቃል የሚገቡበትን ቅጽ በመሙላትና መፈረም ከሚያቀርቡት የዕቃዎች / አገልግሎቶች ዋጋ ዝርዝር ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው::
1.7. ማንኛውም ተጫራች ለሚጫረትበት ዕቃ በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የጨረታ ማስከበሪያ የባንክ ዋስትና /CPO/ የጨረታ ሰነዱ ውስጥ የተጠየቀውን የጨረታ ማስከበሪያ በአጋርፋ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ሥም ማቅረብ አለበት፡፡
-
የጨረታው አሸናፊ ማሸነፉ በተገለጸበት 10 /አስር/ ቀናት ውስጥ የውል ስምምነት ካልፈፀመ ፈቃደኛ እንዳልሆነ ተቆጥሮ ለጨረታው ዋስትና ማስከበሪያ ያስያዘው ገንዘብ ለኮሌጁ ገቢ ይሆናል፡፡
-
በጨረታው ለመካፈል የሚፈልጉ ሕጋዊ ተወዳዳሪዎች ለአንዱ የጨረታ ሠነድ የማይመለስ የኢትዮጵያ ብር 200 /ሁለት መቶ/ ብቻ በጥሬ ገንዘብ በሕጋዊ ሠነድ በመክፈል አዲስ አበባ ኃይሌ ገብረስላሴ ጎዳና በጌታነህ በሻህ ህንፃ በኩል ወደ ቦሌ በሚወስደው መንገድ ከአዲስ ህይወት ሆስፒታል ፊትለፊት በሚገኘው አላጊ የግብርና ቴክኒክ ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ከሚገኘው የአጋርፋ ኮሌጅ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት እና አጋርፋ የግ/ቴ/ሙ/ት/ትና/ሥ/ኮሌጅ ግዥና ፋይናንስ ስራ አስፈፃሚ በአማርኛ ቋንቋ የተዘጋጀውን የጨረታ ሠነድ መግዛት ይችላሉ፡፡
-
ይህ የግዥ ጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ጨረታው መዝጊያ ቀን ድረስ የዋጋ ማቅረቢያቸውን ኦሪጅናልና ኮፒውን በመለያየት ከተያያዥ ሠነዶች ጋር በሰም በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈፃሚ ጽ/ቤት ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል::
-
የጨረታው መክፈቻ ቀን፡-
5.1. ጨረታው ሚያዝያ 06 ቀን 2017 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ሠዓት ተዘግቶ በዕለቱ ከቀኑ 8፡30 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ የኮሌጁ ጉዳይ አስፈጻሚ ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
5.2 የጨረታው መክፈቻ ቀን እንደ አጋጣሚ የህዝብ /ብሔራዊ/ በዓል ከሆነ የጨረታ መዝጊያና መክፈቻ ሰዓት እንደተጠበቀ ሆኖ በቀጣይ የሥራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
ሌላ ተጫራች በሰጠው ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
-
ኮሌጁ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ ይችላል፡፡
ለበለጠ መረጃ፦
ስልክ ቁጥር፡-0116625004 አዲስ አበባ
0922565819/0910316003/ አጋርፋ ኮሌጅ
ፋክስ ቁጥር፡- 0221191154 አጋርፋ ኮሌጅ
ፖስታ ሣ.ቁ-15/211 ባሌ ሮቤ
አጋርፋ የግብርና ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ሥልጠና ኮሌጅ
