የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል በ2017 ዓ/ም በጀት ዘመን ለህግ ታራሚዎች ትምህርትና ስልጠና የሚውሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ የእንጨት ስራ ዕቃዎች፣ የኤሌከትሪከ ዕቃዎች፣ የቧንቧ ዕቃዎች፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ የሽመና ዕቃዎች፣ ጨርቃ ጨርቶች እና አነስተኛ የእጅ መሳሪያዎች ወይም አነስተኛ ማሽኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል
የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ
የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል በ2017 ዓ/ም በጀት ዘመን ለህግ ታራሚዎች ትምህርትና ስልጠና የሚውሉ የተለያዩ ብረታ ብረቶች፣ የእንጨት ስራ ዕቃዎች፣ የኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ የቧንቧ ዕቃዎች፣ የኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ የሽመና ዕቃዎች፣ ጨርቃ ጨርቶች እና አነስተኛ የእጅ መሳሪያዎች ወይም አነስተኛ ማሽኖችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለዚህ ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ ባሉት 15 ቀናት ውስጥ የጨረታውን ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ከግዥ ክንውን ቡድን ክፍል በመግዛት በጨረታው ሰነድ ላይ የምትሸጡበትን ዋጋ በመግለፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማስገባት ማስታወቂያው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
-
ጨረታው በ15ኛው የስራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡15 ሰዓት ይከፈታል፡፡
-
የተገለፀው ቀን ካላንደር የሚዘጋው ሆኖ ከተገኘ ቀጥሎ ባለው የሥራ ቀን ከላይ በተገለፀው ሰዓት የሚዘጋ እና የሚከፈት ይሆናል፡፡
-
ለመወዳደር የሚመጡ ተጫራቶች:-
-
የጨረታ ማስከበሪያ ከሚያቀርቡት ዋጋ ጋር ተመጣጣኝ የሆነ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 100,000.00 /አንድ መቶ ሺህ ብር/ በባንክ በተመሰከረለት ቼከ /CPO/ ብቻ ከጨረታ ሰነዱ ጋር አያይዞ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
-
አግባብነት ያለው የዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ የሚያቀርብ
-
የዘመኑን የመንግስት ግብር ግዴታ መወጣታቸውን የሚገልፅ የድጋፍ ደብዳቤ የሚያቀርብ
-
የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ምዝገባ የምስክር ወረቀት (ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች) የሚያቀርብ
-
በግዥ ኤጀንሲ ድረ-ገፅ (WWWppa.gov.et) የአቅራቢነት ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የሚገልፅ የምስክር ወረቀት
-
በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል የድጋፍ ደብዳቤ
-
ተጫራቾች ለሚጫረቱት እቃ ናሙና (sample) ለሚያስፈልጋቸው ናሙና (sample) ማቅረብ አለባቸው፡፡
-
ለሚጫረቱት እቃ በዘርፉ የተመዘገቡ መሆን አለባቸው፡፡
-
ከላይ እንደተገለፀው ጨረታው በማዕከሉ ቅጥር ግቢ ሁለተኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 32 ተጫራቾች እና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
-
መ/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊል ወይም ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ፦ በስልክ ቁጥር 0464414301 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በፌደራስ ማረሚያ ቤት ኮሚሽን የዝዋይ ተሃድሶ ልማት ማረሚያ ቤት ማዕከል
