Tender Detail

Tender Details

  • Company ጎጆ ብሪጅ ጎሮ ሳይት ብሎክ 4 የመኖሪያ ቤት ሃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር
  • Address ኢትዮጵያ, Phone: 0911209591
  • Website
  • Deadline31 Mar 2025, 12:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening date2025-04-01 00:00:00
  • Categories Accounting & Auditing

ጎጆ ብሪጅ ጎሮ ሳይት ብሎክ 4 የመኖሪያ ቤት ኃላ/የተ/የህ/ሥራ ማኅበር ከተቋቋመበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ድረስ ያለውን የማህበሩን ሒሳብ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የሒሳብ አዋቂዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

ጎጆ ብሪጅ ጎሮ ሳይት ብሎክ 4 የመኖሪያ ቤት ሃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር


 

የሒሳብ ስራ አገልግሎት የጨረታ ማስታወቂያ

 

ጎጆ ብሪጅ ጎሮ ሳይት ብሎክ 4 የመኖሪያ ቤት ኃላ/የተ/የህ/ሥራ ማኅበር በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የህብረት ስራ ኤጀንሲ የህብረት ስራ ማህበራትን ለማቋቋም በወጣ አዋጅ ቁጥር 985/2009 መሠረት በኅዳር 2014 ዓ.ም የተቋቋመ የመኖሪያ ቤት የህብረት ስራ ማህበር ነው:: ማህበሩ ከተቋቋመበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ጥር 30 ቀን 2017 ድረስ ያለውን የማህበሩን ሒሳብ ህጋዊ ፈቃድ ያላቸውን የሒሳብ አዋቂዎች በጨረታ አወዳድሮ ማሰራት ይፈልጋል::

ስለሆነም የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟላ ማንኛውም ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፤

  1. ከኢትዮጵያ ሒሳብ አያያዝና ኦዲት ቦርድ ሒሳብ ለመስራት የሚያስችል የታደሰ የድርጅት ምዝገባ ሰርተፊኬት ማቅረብ የሚችሉ፣
  2. የሒሳብ ስራ ለመስራት የሚያስችል ለዘመኑ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ፣ የግብር ከፋይነት ምዝገባ ሰርተፊኬት እንዲሁም የዘመኑን ግብር ከፍለው በጨረታ ለመሳተፍ የሚያስችል ከግብር ሰብሳቢ መ/ቤት የተሰጠ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው::
  3. ተጫራቾች የሒሳብ ስራውን የሚያከናውንበትን ዋጋ እና የሒሳብ ስራውን ለማጠናቀቅ የሚወስድባቸውን ጊዜ በግልጽ መጥቀስ ይጠበቅባቸዋል::
  4. ተጫራቾች ከላይ የተጠቀሱትን ማስረጃዎችና ዝርዝር ሁኔታዎችን በመሙላት የፋይናንሻል እና የቴክኒካል ሰነዶቻችሁን ለየብቻ በማዘጋጀት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ከታች በተገለጸው አድራሻ በመቅረብ የጨረታ ሰነዱን ማቅረብ ይኖርባቸዋል::
  5. ጨረታው መጀመሪያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ5 (አምስት) ተከታታይ የስራ ቀናት የሚቆይ ሆኖ በሚቀጥለው የስራ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል::

 

ማሳሰቢያ፡- ማህበሩ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::

 

ስለጨረታው ዝርዝር ማብራሪያ ለማግኘት የሚፈልጉ ተጫራቾች በሚከተሉት ስልክ ቁጥሮች ደውለው ማግኘት ይችላሉ::

 

አድራሻ፡- ስልክ ቁጥር- 0911209591 ወይም 0913117795 ወይም 0911480442

 

 

ጎጆ ብሪጅ ጎሮ ሳይት ብሎክ 4 የመኖሪያ ቤት ሃላ/የተ/የህ/ስራ ማህበር

 

Save Tender