የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 007/17
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት ልዩ ልዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ባሉበት ሁኔታ በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
ስለሆንም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሰነድን ለመግዛት ሲመጡ ይህንኑ የሚያረጋግጥ ሰነድ ወይም መታወቂያ ይዘው መቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ከሰኞ እስከ አርብ 2፡00 ሰዓት እስከ 11፡00 ሰዓት የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ አዲስ አባባ በሚገኘው ዋናው መ/ቤት 2ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 207 ሽያጭ ክፍል በመክፈል ደረሰኝ ይዘው ቢሮ ቁጥር 208 ከአቅርቦትና ኮንትራት አስተዳደር ቡድን ቢሮ ሰነዱን መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ንብረቶችን ማየት የሚፈልጉ ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የዝዙበትን ደረሰኝ በመያዝ አዲስ አበባ ዋና ግቢ እና ደብረዘይት ስልጠና ማዕከል በመገኘት ዘወትር በስራ ሰዓት ማየት ይችላሉ።
- ተጫራቾች የሚገዙትን ልዩ ልዩ ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በኢንስቲትዩቱ ስም በባንክ በተረጋገጠ ሲፒአ ወይም በጥሬ ገንዘብ ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ ከጨረታ ሰነዱ ጋር በማያያዝ በታሸገ ኤንቨሎፕ አሽጎ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 /አስራ አምስት/ ተከታታይ ቀን በአየር ላይ ይውል እና በ16ኛው ቀን 4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ቀን 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- የጨረታው መክፈቻ ቀን ቅዳሜ እና እሁድ ወይም የበዓል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው ቀን በተመሳሳይ ሰዓት ይሆናል። ተጫራቾች በራሳቸው ፈቃድ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኙ ቢቀሩ የጨረታውን መከፈት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው መገምገሚያ መስፈርት ዋጋና የተሟላ የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ሲፒኦ) እንዲሁም በሰነዱ የተገለጹትን አሟልቶ መገኘት አለባቸው::
- ልዩ ልዩ ንብረቶች የመነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) ያላስያዘ እና በሠነዱ የተቀመጡን ሌሎች ነጥቦችን ያላሟሉ ተጫራች ከጨረታው ውድቅ ይደረጋሉ፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ያወጣውን የጨረታ ሰነድ በስሙ ላይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል፡፡
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቶች አሸናፊነታቸው ከተገለጸላቸው ቀን ጀምሮ ባሉት 10 የስራ ቀናት ውስጥ ያሸነፉበትን ዋጋ በሙሉ በመክፈል ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡ ሆኖም ሙሉ ክፍያውን በተጠቀሰው ጊዜ ገደብ መክፈል ካልቻሉ ያስያዙት የጨረታ ማስከበሪያ ለኢንስቲትዩቱ ገቢ ይደረጋል፡፡
- ኢንስቲትዩቱ ጨረታውን እንዳስፈላጊቱ በከፊል ወይም በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
አድራሻ፡- አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03 ስልክ ቁጥር 011-6-45-41-47/011-6-45-35-98 /011-8-69-49-31 ከሳሊህተ ምህረት ማርያም ቤቴ/ክርስትያን ፊት ለፊት የሚገኘው ህንፃ
የኢትዮጵያ ስራ አመራር ኢንስቲትዩት
