በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ህዝብ ምክር ቤት አዳራሽ ታጣፊ ወንበር ወይም sinma chiar በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ከልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ህዝብ ምክር ቤት አዳራሽ ታጣፊ ወንበር ወይም sinma chiar በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሠረት ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን።
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፣
- የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፣
- የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፣
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች፤
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው/ላት፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ/ነች፤
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ 100,000 /አንድ መቶ ሺህ/ ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች ናሙና አቅርበው በናሙና መሰረት ማስረከብ ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ዋና እና ኮፒውን በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታዎች ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 9፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በመቅረብ መግዛት ይችላል፡፡
- ጨረታ አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን ታጣፊ ወንበር ወይም sinma chiar በወረዳው ህዝብ ምክር ቤት አዳራሽ ቀርቦ ወንበሮችን ዕውቅና በተረጋገጠ ባለሙያ ማስተከል ይኖርባቸዋል።
- ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-11 ድረስ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን፣ ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጠቀሱትን መስፈርቶችን እንዲያቀርቡ የተጠየቁ ማስረጃዎችን ያላቀረበ እንደሆነ ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ16 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ16ኛው ቀን 4፡30 ታሽጎ በ16ኛው ቀን 5፡00 ይከፈታል፡፡ 16ኛው ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
ማሳሰቢያ
- መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 0910409544 ይደውሉ።
ጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
