Tender Detail

Tender Details


በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች የጽ/መሣሪያ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡


 

የጨረታ ማስታወቂያ

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በመደበኛ በጀት ለወረዳ ሴክተር መ/ቤቶች የጽ/መሣሪያ እና ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ከታች የተጠቀሱትን መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡

    1. ሎት አንድ የጽ/መሣሪያ ግዥ ጨረታ
    2. ሎት ሁለት ኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች ግዥ
  1. በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያለው/ላት፣
  2. የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው/ላት፣
  3. የአቅራቢነት ምዝገባ ምስክር ወረቀት ያለው፤
  4. የዘመኑን ግብር የከፈለ/ለች፤
  5. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው/ላት፣
  6. ተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ/ነች፤
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በእያንዳንዱ ሎት በባንክ የተመሰከረለት ሲፒኦ /CPO/ ወይም ጥሬ ገንዘብ ጨረታው ከመከፈቱ በፊት 10,000 /አስር ሺህ/ ብር ማስያዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡
  8. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-7 የተጠቀሱ ማስረጃዎችን ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ ዋና እና ኮፒውን በማዘጋጀት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታዎች ዘወትር በሥራ ሰዓት ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት እስከ 9፡00 ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
  9. ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የጨረታ ሰነዶችን የማይመለስ 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 14 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ፡፡
  10. ጨረታ አሸናፊው ድርጅት የሚያቀርበውን ዕቃ ወይም ንብረት በወረዳው ፋይናንስ ጽ/ቤት ቀርቦ ማስረከብ ይኖርበታል፡፡
  11. ተጫራቾች ከላይ ከተራ ቁጥር 1-10 ድረስ የተዘረዘሩትን መስፈርቶችን፣ ማስረጃዎችን እና ሁኔታዎችን ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡ የተጠቀሱት መስፈርቶችን እንዲያቀርቡ የተጠየቁ ማስረጃዎችን ያላቀረበ እንደሆነ ይህንን ባለማድረጉ ምክንያት ከውድድር ውጪ ይደረጋል፡፡
  12. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ሎት አንድ ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ15ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በ15ኛው ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ ሎት ሁለት ለ15 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ15ኛው ቀን 9:00 ታሽጎ በ15ኛው ቀን 9:30 ይከፈታል፡፡ 15ኛው ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡

ማሳሰቢያ

መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 0910409544 ይደውሉ።

 

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የጎፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት

Save Tender