በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የነፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ/ም በዋን ዋሽ ብሄራዊ ፕሮግራም በጋዛር ጤና ጣቢያ ግብ ቦኖ ሥራ እና ውሃ መስመር ዝርግ ቆሻሻ ማቃጠያ (Incinrator) ግንባታ፣ ዕንግዴ ልጅ መቅበሪያ (Placent pit) እና ባለሶስት ክፍል መፀዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የነፋ ዞን መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2017 ዓ/ም በዋን ዋሽ ብሄራዊ ፕሮግራም በጋዛር ጤና ጣቢያ ግብ ቦኖ ሥራ እና ውሃ መስመር ዝርግ ቆሻሻ ማቃጠያ (Incinrator) ግንባታ፣ ዕንግዴ ልጅ መቅበሪያ (Placent pit) እና ባለሶስት ክፍል መፀዳጃ ቤት ግንባታ በግልጽ ጨረታ ተጫራቾችን አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ በዚህም መሠረት ከታች በዝርዝር የተቀመጡ መስፈርቶችን የምታሟሉ ተጫራቾች እንድትወዳደሩ እንጋብዛለን፡፡
- ሎት አንድ ጋዛር ጤና ጣቢያ ግቢ ቦኖሥራ እና ውሃ መስመር ዝርግ ጨረታ
- ሎት ሁለት ጋዛር ጤና ጣቢያ ግቢ ቆሻሻ ማቃጠያ (Incinrator) ግንባታ ጨረታ
- ሎት ሶስት ጋዛር ጤና ጣቢያ ግቢ ዕንግዴ ልጅ መቅበሪያ (Placent pit) ግንባታ ጨረታ
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው/ያላት፡
- የምዝገባ ምስከር ወረቀት ያለው/ያላት
- የዘመኑን ግብር የከፈለ/የከፈለች:
- የግብር መክፈያ መለያ ቁጥር /TIN/ ያለው/ያላት
- የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ተመዝጋቢ የሆነ/የሆነች
- የሙያ ፈቃድ GC ወይም BC ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
- ለሎት እንድ የውሃ ስራዎች ግንባታ GC ወይም WWC ፍቃድ ማቅረብ የሚችል/የምትችል፣
- የመልካም ሥራ አፈፃፀም ማስረጃ ማቅረብ የሚችል/የምትችል;
- የግንባታ ቦታ የጎበኙበት ደብዳቤ ከአሰሪው መ/ቤት ማቅረብ የሚችል/የምትችል፤
- የጨረታ ማስከበሪያ CPO ወይም በጥሬ ገንዘብ 10,000 /አስር ሺህ ብር/ ማስያዝ የሚችል/የምትችል፤
- ደረጃ ሰባት እና በላይ (አንድ እስከ ሰባት)
- የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ በመክፈል መግዛት ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች ከላይ ከ1-12 የተጠቀሱትን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዳቸው ጋር በማያያዝ በታሸገ ፖስታ ለዚሁ በተዘጋጀው ጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘወትር በመንግስት የሥራ ሰዓት ማስገባት ይኖርበታል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ማስታወቂያው በግልጽ ጨረታ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ22ኛው ቀን 4፡00 ታሽጎ በ22ኛው ቀን 4፡30 ሎት አንድ ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ ይከፈታል፣ ሎት ሁለት ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ22ኛው ቀን 8፡00 ታሽጎ በ22ኛው ቀን 8፡30 ይከፈታል፡፡ ሎት ሶስት ለ21 ተከታታይ የሥራ ቀናት የሚቆይ ሲሆን የጨረታ ሣጥኑ በ22ኛው ቀን 9:30 ታሽጎ በ22ኛው ቀን 10፡00 ይከፈታል፡፡ 22ኛው ቀን ቅዳሜና ዕሁድ ወይም በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፣
ማሳሰቢያ
መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው:: ስለጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ በስልክ ቁጥራችን 0916767044 ወይም 0910409544 ይደውሉ፡፡
መሎ ኮዛ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት
