የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ባሉበት በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር ገ/ላ/ኢ/03/2017 ግራንድ በላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ
በድጋሚ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ
የተለያዩ ያገለገሉ እቃዎች ባሉበት በግልጽ ጨረታ ለመሸጥ የተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ ቁጥር ገ/ላ/ኢ/03/2017 ግራንድ በላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን
ሎት 1፡ ባለ 6 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ጥቅል ብረት
ሎት 2፡ ከ2-9 ሜትር ርዝመት ያላቸው ከ8 -16 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር የሆኑ ቴንድኖ ብረቶች
ሎት 3፡ ከ2-7 ሜትር ርዝመት ያለው ባለ 20 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር ቴንድኖ ብረት
ሎት 4፡ 2 ሜትር በታች የተቆራረጡ ከ6- 20 ሚሊ ሜትር ዲያሜትር የሆነ ቴንድኖ ብረቶች
ሎት 5 ፡ አገልግሎት የሰጡ የቢሮና የግንባታ እቃዎች
ሎት 6፡ የተለያዩ እቃዎች ቁርጥራጭ ብረት
ሎት 7 ፡ ባለ 28 ጌጅ 3 ሜትር ርዝመት ያለው የጣራ ቆርቆሮ
ሎት 8 : ባለ 28 ጌጅ 5 ሜትር ርዝመት ያለው የጣራ ቆርቆሮ
ሎት 9፡ አገልግሎት የሰጡ የላሜራ በር
ሎት 10 : ያገለገለ የብረት አልጋ
እቃዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሸጥ ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተጫራቾች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ነጥቦች በማሟላት ቀርበው መወዳደር ይችላሉ፡፡
- በጨረታው የሚወዳደሩ ተጫራቾች ኢትዮጵያዊ ዜግነት ያላቸው ሆነው ሰነድ ለመግዛት ሲመጡ ይህንን የሚያረጋግጥ መታወቂያ ይዘው መቅረብ አለባቸው፡፡ ድርጅት ከሆነ በድርጅቱ ስም መመዝገብ ይኖርበታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ድረስ ወልድያ ዩኒቨርሲቲ ከሚገኘው የግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 1 በመሄድ 400 (አራት መቶ ብር ) በመክፈል መግዛት የሚችሉ ሲሆን በተጨማሪም ቡና ባንክ (አዲስ አበባ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ ፤ ባህርዳር ፣ ባህርዳር (ጊዮርጊስ አካባቢ) ቅርንጫፍ ፤ ደሴ ፣ ጦሳ ቅርንጫፍ፣ ኮምቦልቻ ኮምቦልቻ ቅርንጫፍ ፤ ወልድያ ወልድያ ቅርንጫፍ) በመሄድ በግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ቡና ባንክ ሂሳብ ቁጥር 15596001000213 ገቢ በማድረግ መውሰድ ይችላሉ፡፡ ክፍያ ሲከፍሉ ከባንክ ከሆነ አድቫይስ ከኢንተርፕራይዙ ቢሮ ከሆነ ደረሰኝ መቀበልና መመዝገብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚገዙትን ንብረቶች የጨረታ መነሻ ዋጋ 2 በመቶ (2%) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ፣ የዋጋ መሙያ ፣ የጨረታ ሰነድ የገዙበትን የባንክ አድቫይስ (ደረሰኝ) እና በጨረታ ሰነዱ ላይ የተገለጸውን የቃለ መሃላ ቅፅ በታሸገ ኤንቨሎፕ በማድረግ ኦርጂናልና ኮፒ ዶክመንት ለየብቻው አድርገው በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ ቢሮ ቁጥር 1 በተዘጋጀ የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከመዘጋቱ በፊት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ቼክና ኢንሹራንስ ማቅረብ አይቻልም (የተከለከለ ነው)፡፡
- ተጫራቾች ከላይ በተራ ቁጥር 3 የተገለፁትና አሟልተው ከተገኙ የሚወዳደሩት በሞሉት ነጠላ ዋጋ ብቻ ይሆናል፡፡
- የጨረታ ሳጥኑ ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በዚያኑ ቀን በ4፡15 ሰዓት ተጫራቾች ወይምሕጋዊወኪሎቻቸው በተገኙበት በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላለበላ ኢንተርፕራይዝ መሰብሰቢያ አዳራሽ ይከፈታል፡፡ ሆኖም የመክፈቻ ቀኑ ቅዳሜና እሁድ ወይም የበዓላት ቀን ከዋለ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ተጫራቹ በራሱ ምርጫ ጨረታው በሚከፈትበት ጊዜ ሳይገኝ ቢቀር የጨረታውን መከፈትን አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታ ሰነዱን በስሙ ሳይገዛ የተወዳደረ ማንኛውም ተጫራች ከተገኘ ከውድድር ውድቅ ይደረጋል።
- በጨረታው አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ንብረቶች ሙሉ ክፍያ ከፍሎ እስከሚወስድ ድረስ ለውል አስተገባበር ዋስትና የሚሆን የጠቅላላ ዋጋውን 10 በመቶ በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ማስያዝ አለበት።
- አሸናፊው ተጫራች ያሸነፈውን እቃ በሚረከበው የዕቃ መጠን ክፍያ እየፈጸመ ንብረቶቹን ውል በያዘ በ20 ቀናት ውስጥ የማንሳት ግዴታ አለበት፡፡
- አሸናፊው ተጫራች የእቃውን የሚዛን ፣ የጫኝ አውራጅና ትራንስፖርት በራሱ ይሆናል፡፡
- ኢንተርፕራይዙ ጨረታውን ለመቀበል ወይም ላለመቀበል የሚችል ሲሆን በማናቸውም ጊዜ ጨረታውን ለመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ተጨማሪ ማብራሪያ ካስፈለገ በስልክ ቁጥር 09-20-47-80-39 ወይም 09-13-07-25-07
በወልድያ ዩኒቨርሲቲ ግራንድ ላሊበላ ኢንተርፕራይዝ
