በደ/ም/ኢ/ህ/ ክልላዊ መንግስት የቴፒ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ፣ የአውቶሞቲቭ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ የብረታ ብረት፣ አይሲቲ እና ጋርመንት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በ/ደ/ም/ኢ/ሕ/ክ/መ/ክ/ቴክ/ቢሮ የቴፒ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ
ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የግዥ መለያ ቁጥር ግ/ጨ/ማ/01/2017 ዓ.ም
በደ/ም/ኢ/ህ/ ክልላዊ መንግስት የቴፒ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ለ2017 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ፣ የአውቶሞቲቭ ዕቃዎች፣ የደንብ ልብስ፣ ኤሌክትሪክ ዕቃዎች፣ ኮንስትራክሽን ዕቃዎች፣ የብረታ ብረት፣ አይሲቲ እና ጋርመንት ዕቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልግ ማንኛውም ሕጋዊ የሆነ ተጫራች ከዚህ በታች በተዘረዘሩት መስፈርቶች መሰረት መወዳደር ይችላል፡፡
በመሆኑም፤
- የዘመኑን በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፡፡
- የንግድ ምዝገባ ሰርተፍኬት ማቅረብ የሚችል፡፡
- የቫት ተመዝጋቢ የሆነ፡፡
- በመንግስት ግዥ ለመሳተፍ በተጫራቾች የእቃ አቅራቢነት ምዝገባ የተመዘገበ፡፡
- የሚቀርበው ዋጋ ቫትን ያካተተ ወይም ያላካተተ መሆኑን ገላጭ ነገር መኖር አለበት፡፡
- ተጫራቾች ለጨረታ ማስከበርያ የሚሆን ብር 5000 ሺህ ከታወቀ ባንክ በሲፒኦ /CPO/ ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት ባሸነፈው ገንዘብ ልክ ለውል ማስከበርያ 10% ማስያዝ ይኖርበታል፡፡
- የጨረታ ሰነዱ ሳጥን ውስጥ የሚገባውም ሆነ የሚከፈተውም በኮሌጁ ቅጥር ግቢ ይሆናል፡፡
- አሸናፊ የሆነ ድርጅት ንብረቱን እስከ ኮሌጁ ግቢ ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለበት፡፡
- በአንዱ ጨረታ ዋጋ ላይ ተንተርሶ ዋጋ ማቅረብ አይቻልም፡፡
- ከተጫራቾች የዕቃውን ዋጋ መሙላት ያለባችሁ ኮሌጁ ባዘጋጀው የጨረታ ሰነድ ላይ ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን በፖስታ በማሸግ በወቅቱ ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ ለተከታታይ 15 ቀናት የሚቆይ ሲሆን ጨረታው በመጨረሻ ቀን 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በእለቱ 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡ ነገር ግን የሚታሸግበት ቀን ወይም የሚከፈትበት ቀን ከስራ ቀን ውጪ ከሆነ በቀጣይ ስራ ቀን 4፡00 ታሽጎ በዚያው እለት 4፡30 ላይ ይከፈታል፡፡
- ዝርዝር የጨረታ ሰነዱን ከቴፒ/ቴ/ሙ/ት/ስ/ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር-910 በመቅረብ የማይመለስ ብር 50 በመክፈል መግዛት ይቻላል፡፡
- የተሞላው ዋጋ ስርዝ ድልዝ ከሆነ ከዋጋው ፊት ለፊት በፊርማ ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፡፡ ነገር ግን ይህ ሳይሆን ቀርቶ ሰነዱ ተሞልቶ ቢመጣ ስርዝ ድልዝ ያለበት የተሞላው ዋጋ ከጨረታ ውጪ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በእለቱ /በሰዓቱ/ ባይገኙም የኮሌጁ ጨረታ ኮሚቴ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- ኮሌጁ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ኮሌጁ ከአዲስ አበባ 611 ኪሎ ሜትር ሲሆን 74 ኪሎ ሜትሩ ፒስታ መንገድ መሆኑ ይታወቃል።
በደ/ም/ኢ/ህ/ክልላዊ መንግሥት በሸካ ዞን የቴፒ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
ለበለጠ መረጃ፡- ስልክ ቁጥር:- 047 556 11 02
የቴፒ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ
