በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት የተለያዩ ግንባታዎችን ተጫራቾች በማወዳደር በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጋርዱላ ዞን የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ከሚፈፅሟቸው ግዥዎች መካከል፡-
ሎት 1. በጊዶሌ ከተማ የኮብል/ገጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ግንባታ /Project A/
ሎት 2. በጊዶሌ ከተማ የኮብል/ገጠኛ ድንጋይ ንጣፍ ግንባታ /Project B/
ሎት 3. በጊዶሌ ከተማ የኮብል/ገጠኛ ንጣፍ ግንባታ /Project C/
ሎት 4. በጊዶሌ ከተማ የመንገድ ቱቦ ቀበራ ግንባታ /Project A/
ሎት 5. በጊዶሌ ከተማ ዲችና ሪተይንግ ዎል ግንባታ /Project B/
ሎት 6. በጊዶሌ ከተማ ዲች ጥገናና ቱቦ ቀበራ ግንባታ /Project A1/ እና
ሎት 7. የቧንቧ ዕቃዎችን ከዚህ በታች የተዘረዘሩ መስፈርቶችን ከሚያሟሉ
ተጫራቾች በብሔራዊ ግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት/ማስገንባት ይፈልጋል፡፡
በዚህ መሠረት፡-
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
- የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ
- የአቅራቢነት ምዝገባ የምስክር ወረቀት /ኦን ላዬን/ ያላቸው
- የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር TIN No ያላቸው
- በግንባታ ላይ የሚሳተፉ ተጫራቾች ደረጃ 8 እና ከዛ በላይ በማሳደስ ማቅረብ አለባቸው። የጨረታ ማስከበሪያ የቧንቧ ዕቃዎች ሃያ ሺህ ብር ለግንባታ ሃምሳ ሺህ ብር ሲ.ፒ.ኦ በቼክ ከሆነ ከባንክ ደብዳቤ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የጨረታውን ሰነድ ከጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ገቢዎች ቅ/ጽ/ቤት የማይመለስ 1 በመክፈል መግዛት አለባቸው፡፡
- የገዙትንም ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ በማዘጋጀት በሁለት በተለያዩ ፖስታ በማሸግ ኦርጅናልና ኮፒ አዘጋጅቶ ፊርማና ማህተም በማሳረፍ ይህ ማስታወቂያ በዚህ ጋዜጣ ከታወጀበት ቀን ጀምሮ በ15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለቧንቧ ዕቃዎች በ15ኛው ቀን እስከ 4:00 ብቻ መግባት ያለበት ሲሆን ለግንባታው 21 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ለዚህ በተዘጋጁ ሣጥን ውስጥ እስከ 4፡00 ብቻ ማስገባት አለባቸው:: 15ኛው/21ኛው የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይከፈታል፡፡
- ጨረታው በዕለቱ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4:30 ላይ በጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ይከፈታል፡፡
- የተጫራቾች በሰዓቱ ያለመገኘት የጨረታውን አከፋፈት አያስተጓጉልም፡፡
- የጨረታው አሸናፊዎች ተለይተው በተገለፁ 7 ቀናት በኋላ በ5 ቀናት ውስጥ አሸናፊዎች የውል ማስከበሪያ 10% ወይም ከዛ በላይ ሊጠየቅ ስለሚችል በማስያዝ ውል መግባት ያለባቸው ሲሆን ተሸናፊዎች ደግሞ ያስያዙትን የጨረታ ማስከበሪያ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- አሸናፊዎች በገቡት ውል መሠረት ዕቃዎቹን እስከ ጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት ድረስ የማቅረብ ግዴታ አለባቸው::
- በጨረታ ሰነድ ላይ የተሞሉ ዋጋዎች ለዕቃ አቅርቦት እስከ 35 ቀናት ፀንተው መቆየት ይኖርባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ ከጨረታው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ስልክ ቁጥር፡- 046-7-74-05-64/536 ይደውሉ
የጊዶሌ ከተማ አስተዳደር ፋ/ጽ/ቤት
