የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፍልጋል።
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ንብረት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ
ያገለገሉ ንብረቶች ሽያጭ የጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ የተለያዩ ያገለገሉ ንብረቶችን ማለትም፡
1. ልዩ ልዩ ፈርኒቸሮች ማለትም የእንግዳ ወንበሮች፣ ኮመዲናዎች፣ ጠረጴዛዎች ሶፋዎች፤
2. የኤሌክትሪክ እቃዎች፤
3. የመኪና ጎማዎች፣ ከመነዳሪዎች፤
ስለዚህ ፦
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ ብር 5,000.00 (አምስት ሺህ ብር) ከዋናው ሰነድ ጋር በማያያዝ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 (አስራ አምስት) ተከታታይ ቀናት ውስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) በአስተዳደር ህንጻ ባለው ብሎክ 02 የፋይናንስ ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ በመክፈል እና የከፈሉበትን ደረሰኝ በብሎክ 12 አንደኛ ፎቅ በሚገኘው የንብረት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ በማቅረብ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የመወዳደሪያ ሃሳባቸውን የያዘ የዋጋ ሰነድ (Financial Document) ዋናና ቅጅ (original and copy) ተለይቶ በታሸገ ፖስታ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት እስከ 16ኛው ቀን 4፡00 ሠዓት ብቻ በዩኒቨርሲቲው ንብረት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ለዚህ ተብሎ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ ቀናት በ16ኛው ቀን በ4፡00 ሰዓት ተዘግቶ በ4፡30 ሰዓት ላይ ይከፈታል።
- የጨረታው መክፈቻው 16ኛው ቀን የሳምንቱ የእረፍት ቀን ወይም ብሄራዊ በዓል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተገለጸው ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች በሌላ ተጫራች ዋጋ ላይ ተመስርተው የመወዳደሪያ ዋጋ ማቅረብ አይችሉም፡፡
- ተጫራቾች ያሸነፉትን እቃ በሙሉ ማሸነፋቸው በተገለጸላቸው 10 ቀናት ውስጥ በራሳቸው ወጭ ቆጥረውና ጭነው ማንሳት ይኖርባቸዋል፡፡
- ዩኒቨርሲቲው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡- የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ አዲስ አበባ ሰሚት ኖክ ማደያ አጠገብ፡፡
የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ንብረት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ
