በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በቦሌ ክፍለ ከተማ በወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
ሁስተኛ ዙር ግልፅ ጨረታ የእቃ ግዢ ማስታወቂያ
የግዢ ጨረታ መለያ ቁጥር 002/2017
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ ወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሎቶች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በዚህ መሰረት ጨረታውን ለመሳተፍ የሚፈልጉ ህጋዊ ተጫራቾች የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ መሆን አለባቸው።
- ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበትን ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- በገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚ/ር በአቅራቢነት የተመዘገበና ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
- የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያለው፣
- ተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስከር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- ተጫራቾች ከዚህ በታች የተጠቀሰውን የጨረታ ማስረከቢያ በባንክ የተረጋገጠ CPO ብቻ ማቅረብ አለባቸው።
|
ሎት ቁጥር |
የሎት ዝርዝር |
የተጠየቀው የጨረታ ማስከበሪያየኢትዮጵያ ብር |
|
ሎት 1 |
የደንብ ልብስ |
ብር 1,500 |
|
ሎት2 |
አላቂ የቢሮ እቃዎች |
ብር 3,600 |
|
ሎት3 |
አላቂ የትምህርትእቃዎች |
ብር 2,000 |
|
ሎት4 |
የህትመት ስራዎች |
ብር 6,800 |
|
ሎት5 |
የፅዳት እቃዎች ብር |
ብር 18,000 |
|
ሎት7 |
ህንፃና ቁሳቁስ ጥገናእቃዎች ብር |
ብር 10,000 |
|
ሎት9 |
አላቂ የህከምና እቃዎችብር |
ብር 3,000 |
- የጨረታ ሰነዱን ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ የማይመለስ ብር 50.00 (አምሳ ብር) በመክፈል የተዘጋጀውን ሰነድ ከተቋሙ ቢሮ ቁጥር 04 እየቀረቡ መግዛት ይችላሉ።
- ተጫራቾች ጨረታ ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉት 10 (አስር) ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ 04 ድረስ በመምጣት ዋጋው የተሞላበትን የጨረታ ሰነዱን ዋናውንና ፎቶ ኮፒ ለየብቻው በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
- ጨረታው በ10ኛው ቀን በእለቱ 5፡00 ታሽጎ 5፡30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ የስራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል።
- ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዋጋ የውል ማስከበርያ 10% ማስያዝ አለባቸው።
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበት ናሙና ለሚቀርብባቸው እቃዎች ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ናሙና ለማይቀርብባቸው ቋሚ እቃዎች መስሪያ ቤቱ ባቀረበው ስፔስፊኬሽን መሠረት ማቅረብ አለባቸው።
- የጨረታው አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን እቃ በራሱ ትራንስፖርት የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት ድረስ ማቅረብ ይኖርበታል።
- ት/ቤቱ ለጨረታ ከቀረበው ዕቃ እስከ 20% የመቀነስም ሆነ የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ት/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው። አድራሻ፡- ከቦሌ ድልድይ 400 ሜትር ገባ ብሎ ቦሌ ሆምስ ፊት ለፊት ስልክ፡- 011 8 21 77 36
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በቦሌ ከፍለ ከተማ በወረዳ 13 የቦሌ ህብረተሰብ ቅድመ 1ኛ፣ 1ኛ እና መካከለኛ ደረጃ ት/ቤት
