በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ የደብረብርሃን ቅ/ፅ/ቤት ለጽ/ቤቱ ሰራተኞች የሚሆን የደንብ ልብስ ለመግዛት በዘርፉ የተሰማሩ ነጋዴዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ሀ. ብትን ጨርቅ ሎት 1 ለ. የተዘጋጁ ልብሶች ሎት 2
ሒ. የቆዳ ጫማ ሎት 3 መ. የፕላስቲክ ቦቲ ጫማ ሎት 4
ስለሆነም ተጫራቾች:-
- በዘርፉ የተሰማሩ ፍቃዳቸውን ያሳደሱ፣ የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /Tin/ ያላቸውና የተጨማሪ እሴት /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፡፡ ጨረታው ከሁለት መቶ ሺህ ብር በላይ ከሆነ ግዴታ የቫት ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው:: ነገር ግን ከሁለት መቶ ሺህ ብር በታችም ቢሆን ግዴታ የቲኦቲ ተመዝጋቢ መሆን አለባቸው፡፡ በፔድ ደረሰኝ የማናስተናግድ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
- ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1 የተጠቀሱትንና ሌሎች የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዱ ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- በጨረታው የሚቀርበውን ሁሉንም ዝርዝር መግለጫ/ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ /ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ/ የማይመለስ ብር 100 /አንድ መቶ ብር/ ለእያንዳንዱ ጨረታ ሰነድ በመከፈል በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 10 መግዛት ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድ ቦንድ/ የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 2% በባንክ በተረጋገጠ ትእዛዝ /cpo/ ወይም በመስሪያ ቤቱ አካውንት ገቢ አድርገው የባንከ አድቫይዝ ማስያዝ ይችላሉ፣ ከዚህ ውጭ የማንቀበል መሆኑን እንገልፃለን ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ 2% የሚያሲዙት ቫትን አካቶ ነው፤ ግዥው ከብር 10.000.00 /አስር ሺህ ብር/ በላይ ከሆነ ኢንተርፕራይዙ TOT /2%/ የሚሰበስብ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ዋጋውን በኦርጅናል ዋጋ ማቅረቢያ ቅጽ የሚያቀርቡበትን ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ፤ ስምና አድራሻቸውን በመጻፍ ፈርመው ማህተም በማድረግ የጨረታ ፖስታውን በማሸግ በአማራ ደን ኢንተርፕራይዝ ደብረ ብርሃን ቅ/ጽ/ቤት የደንብ ልብስ ግዥ ግልፅ ጨረታ” ተብሎ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ጨረታው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ (ቅዳሜን ግማሽ ቀን ጨምሮ/ እስከ መጨረሻው ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡ ጨረታው በዚሁ ዕለት 4፡00 ሰዓት ላይ ሳጥኑ ታሽጎ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት /ባይገኙም/ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የሚጫረቱበት ነጠላና ጠቅላላ ዋጋ ተእታ 15% ይጨምራል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
- አሸናፊው ተጫራች ሁሉንም ያሸነፉትን እቃዎች በራሱ ትራንስፖርት ኢንተርፕራይዙ በሚገኝበት ቦታ ድረስ ማቅረብ አለበት፡፡
ሁሉም ጨረታ በሎትና በድምር ዋጋ በመሆኑ ማንኛውም ተጫራች የሁሉንም እቃ ዋጋ መሙላት የሚጠበቅበት ሲሆን ሳይሞላ የተዘለለ እቃ ካለ ከውድድር ውጭ ይደረጋል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡- በስልክ ቁጥር 0116375030/0932497118 ደውለው ይጠይቁ፡፡
በአደኢ የደብረ ብርሃን ቅ/ፅ/ቤት
