የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት ለ 2 ዓመት የሚቆይ የቀላል (ትናንሽ) ተሽከርካሪዎች ጥገና የአገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
Debre Markos University (ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ)
የጨረታ ማስታወቂያ
ደ/ማ/ዩ/ብግጨ/24/2017
የደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በ2017 በጀት አመት ከመንግስት በተፈቀደለት በጀት ለ 2 ዓመት የሚቆይ የቀላል (ትናንሽ) ተሽከርካሪዎች ጥገና የአገልግሎት ግዥ በብሄራዊ ግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው መሳተፍ የሚችሉ ከዚህ በታች ማለትም፤
- በዘመኑ እና በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፈቃድ እና የግብር ከፋይነት የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችል፤ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢት እና የግብር ክሊራንስ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤
- ለጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ማለትም ብር 50,000.00 (ሃምሳ ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ ወይንም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንክ ዋስትና በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ስም አሰርቶ ማቅረብ የሚችሉ ተጫራቾች ሁሉ የጨረታ ዶክመንቱን ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ15 ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300.00/ ሶስት መቶ ብር/ በመከፈል መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በተከታታይ 15 ቀን አየር ላይ ቆይቶ በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ በዚያው እለት ከጠዋቱ 4:30 ተጫራቾች ወይንም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የጨረታውን ፋይናሽያል ዶክመንት እንዲሁም የጨረታ ማስከበሪያውን ለየብቻ አስተማማኝ በሆነ ማጣበቂያ በታሸገ ፖስታ በማድረግና በእያንዳንዱ ፖስታ ላይ የመ/ቤቱን ሙሉ ስምና አድራሻ በመፃፍ ማህተም በማድረግ በተጠቃለለ አንድ ፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
- አሸናፊው ድርጅት አሸናፊነቱ በተገለፀለት ከ7 ተከታታይ የስራ ቀናት በኋላ በግንባር ቀርቦ አሸናፊ የሆነበትን ጠቅላላ ዋጋ 10% የውል ማስከበሪያ በማስያዝ በ8 ቀናት ውስጥ ውል መያዝ አለበት፡፡
- ተወዳዳሪዎች የጨረታ ሰነዱን በአግባቡ በመሙላትና በማሸግ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ድረስ በመቅረብ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከተከታታይ 15 ቀናት በኋላ በ16 ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡59 ድረስ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ሲኖርባቸው ጨረታው በዚሁ እለት ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ላይ ተዘግቶ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት 4፡30 ላይ በደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ ህንፃ ቁጥር 27 ቢሮ ቁጥር 10 ውስጥ ይከፈታል። ሆኖም ተጫራቾች በጨረታው ላይ መገኘት ካልቻሉ መስፈርቱን እስካሟሉ ድረስ በጨረታው ላይ ያልተገኙ ተጫራቾች ፖስታ ጨምሮ በእለቱ ይከፈታል፡፡
የበለጠ መረጃ፡- ለማግኘት በስልክ ቁጥር 058 771 66 91/058/178 00 37/ ደውለው መጠየቅ ይችላሉ
❖ የጨረታ መክፈቻ ቀኑ የበአል ቀናት ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን የሚከፈት ይሆናል፡፡ ዩኒቨርሲቲው ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ
