Tender Detail

Tender Details

  • Company በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት
  • Address ቱለፋ ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሃን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ገነት ከተማ አለፍ ብሎ ፡ አማራ ክልል ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 0973 80 72 93
  • Website
  • Deadline11 Mar 2025, 9:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Construction Machinery

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሚያሰራው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ቆረጣ ስራ የሚሆን የማሽን ኪራይ አገልግሎት ግዥ ያስችል ዘንድ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች እና ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት


 

ለሁለተኛ ጊዜ ወጣ የግልፅ ጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ቁጥር 04/17

 

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ፅ/ቤት ለከተማ አስተዳደሩ ከተማና መሰረተ ልማት ጽ/ቤት በ2017 በጀት ዓመት ለሚያሰራው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ቆረጣ ስራ የሚሆን የማሽን ኪራይ አገልግሎት ግዥ ያስችል ዘንድ በዘርፉ የተሰማሩ ህጋዊ ነጋዴዎች እና ተጫራቾችን አወዳድሮ ለመከራየት ይፈልጋል፡፡

ስለዚህ ተጫራቾቾ ፤

  1. በዘመኑ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፤
  2. የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር /TIN/ ያላቸው እና የታደሰ የንግድ ምዝገባ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፤
  3. የግዥው መጠን ብር 200,000 / ሁለት መቶ ሺህ ብር/ እና በላይ ከሆነ የተጨማሪ እሴት ታክስ /VAT/ ከፋይነት የተመዘገቡ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው።
  4. ተጫራቾች በጨረታ ለመሳተፍ ከላይ በተራ ቁጥር 1-3 የተጠቀሱትንና የሚመለከታቸውን ማስረጃዎች ፎቶ ኮፒ ከመጫረቻ ሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
  5. የማሽን ኪራይ አይነት ዝርዝር መግለጫ /ስፔስፊኬሽን/ ከጨረታ ሰነዱ ማግኘት ይችላሉ።
  6. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን የማይመለስ ብር 200 /ሁለት መቶ ብር/ ብቻ በመክፈል ከግዥ/ን/አስ/ቡድን ቢሮ ቁጥር 6 ማግኘት ይችላሉ።
  7. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና /ቢድቦንድ/ ለሚወዳደሩበት የእቃውን ጠቅላላ ዋጋ 1.5% በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ትዕዛዝ /ሲ.ፒ.ኦ/ ወይም በጥሬ ገንዘብ ማስያዝ ይችላሉ።
  8. ማንኛውም ተጫራች የጨረታ ሃሳቡን በአንድ ወይም አንድ ወጥ በሆኑ ሁለት ቅጅዎች ማለትም ዋናና ቅጅ በማለት በጥንቃቄ በታሸገ ፖስታ በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስታወቂያው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በስራ ሰዓት እስከ 16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ድረስ ማስገባት ይኖርባቸዋል።
  9. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት ቢሮ ቁጥር 6 በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡30 ታሽጎ በዛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ይከፈታል፤ 16ኛው ቀን በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል።
  10. መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  11. የሂሳብ ስሌት (አርቲሜቲክ ቼክ) በግዥ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ባለሙያ ከሚስተካከለው ውጪ በተጫራቾች የሚቀርበው የመጫረቻ ሰነድ ላይ በነጠላ እና ጠቅላላ ዋጋ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ተጫራቹ ከጨረታ ውጭ ይሆናል።
  12. በጨረታው ለመሳተፍ የሚፈልጉ ስለ ጨረታው ዝርዝር መረጃ ከፈለጉ ቢሮ ቁጥር 6 ድረስ በአካል በመገኘት ወይም በስልክ ቁጥር 094 808 8732/097 380 7293 በመደወል ማግኘት ይችላሉ።

 

አድራሻ ፡- ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ብርሀን በሚወስደው መንገድ ከአዲስ አበባ 65 ኪ.ሜ ርቀት ከፍቼ ከተማ አለፍ ብሎ እንገኛለን።

 

 

በአማራ ክልል በሰሜን ሸዋ ዞን የቡ/ከ/አስ/ገንዘብ ጽ/ቤት

ቱለፋ

 

Save Tender