በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 01 የጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ሎት1. ደንብ ልብስ ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ ሎት 3. አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 4. የፅዳት እቃዎች ፣ ሎት 5. ቋሚ እቃዎች ፣ ሎት 6. የልብስ ስፌት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
ግልፅ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር : 02/2017
በአራዳ ክ/ከተማ በወረዳ 01 የጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚያስፈልገውን ሎት1. ደንብ ልብስ ፣ ሎት 2. አላቂ የቢሮ እቃዎች ፣ ሎት 3. አላቂ የትምህርት እቃዎች ሎት 4. የፅዳት እቃዎች ፣ ሎት 5. ቋሚ እቃዎች ፣ ሎት 6. የልብስ ስፌት በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡ በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት እና ማቅረብ ይኖረባቸዋል፡፡
- በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፈቃድና የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው እና የስራ መስኩ በጀረባ ገፅ ይመልከቱ የሚለውን በትክክል የሚገልፅ መሆን አለበት።
- የመንግስት ግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑና የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው::
- የጨረታ ሰነዱን ጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የግዥ ቡድን ቢሮ ቁጥር 11 ማስታወቂያው ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀን ከላይ የተዘረዘሩትን መረጃዎችን የምታሟሉ ተጫራቾች በስራ ቀን የጨረታ ሰነዱን መውሰድ ትችላላችሁ።
- ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ዘወትር በስራ ሰዓት በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ/ት/ቤት በመገኘት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በመክፈል የጨረታ ሰነድ ከፋይናንስ ቢሮ መግዛት ይችላሉ፡፡
- የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና የሚያገለግል ዋጋ 2% ሲፒኦ በጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ/ት/ቤት ስም ሲፒአ ወይም በጥሬ ገንንዘብ በማዘጋጀት ማረጋገጫውን ከመወዳደሪያ ሰነዶቻቸው ጋር በፋይናንስ ቢሮ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ስርዝ ድልዝ ኖሮት ካልተፈረመ /በፍሉድ የጠፉ/ ሰነዱ ከጨረታው ይሰረዛል፡፡
- ስፔስፊኬሽን ያልወጣላቸው ዕቃዎች ናሙና ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል ፡፡
- ጨረታው በጋዜጣ ከወጣበት በ11ኛው የስራ ቀን በ4፡00 ሰዓት ላይ ታሽጎ 4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- የገዙትን የጨረታ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ከገዙት የጨረታ ሰነድ ውጭ ተሞልቶ የመጣ ሰነድ ዋጋ የለውም ::
- መ/ቤቱ ለግዥው የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- ዋናው ፖስታ ቤት ከፍ ብሎ ትራኮን ህንፃ ፊት ለፊት /ሊሴ/ገ/ማርያም ት/ቤት ጎን
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር፡- +2511-1-26-28-39
በአራዳ ክፍለ ከተማ ትምህርት መምሪያ የጥቁር አንበሳ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
