በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኝ የልደታ ሰላም የመ/ደ/ት/ቤት የ2017 ዓ.ም አገልግሎት ላይ የሚውሉ የተለያዩ ዕቃዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።
የልደታ ሰላም የመጀመሪያ ደረዳ ት/ቤት
የጨረታ ማስታወቂያ
በልደታ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ስር የሚገኝ የልደታ ሰላም የመ/ደ/ት/ቤት የ2017 ዓ.ም ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የሚፈልጋቸውን ፡-
1. ሎት 1 የደንብ ልብስ 4. ሎት 4 አላቂ የትምህርት ዕቃዎች
2. ሎት 2 አላቂ የቢሮ ዕቃዎች 5. ሎት 5 ልዩ ልዩ መሳሪያዎች
3. ሎት 3 አላቂ የህክምና ዕቃዎች 6. ሎት 6 ለህንፃና ለቁሳቁስ ለተገጣጣሚ መግዣ
መስሪያ ቤቱ ባወጣው ግልፅ ጨረታ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች መወዳደር ይችላሉ
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ላላቸው ተጫራቾችና የታደሰ ንግድ ፈቃድ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ግዢና ንብረት አስተዳደር ኤጀንሲ ድረ ገፅ በአቅራቢዎች ዝርዝር የተመዘገቡ፣ የቲንና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ፣
- የጨረታ አሸናፊዎች የጨረታ ዋስትና 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት እለት አንስቶ በተከታታይ 10 የስራ ቀናተ የማይመለስ 200 ብር (ሁለት መቶ ብር) በልደታ ሠላም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በመገኘት በቢሮ ቁጥር 5 በመምጣት የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሠነዶቻቸውን በታሸገ ኤንቨሎኘ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ በተከታታይ 10 የስራ ቀናት በልደታ ሠላም የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 6 በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታውን ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ10ኛው ቀን ከቀኑ 10፡00 ላይ ታሽጎ በዛኑ ቀን ከቀኑ 10:30 ላይ በልደታ ሠላም የመ/ደ/ት/ቤት በቢሮ ቁጥር 13 ይከፈታል፡፡
- የመከፈቻው ቀን ቅዳሜና እሁድ ወይም የበአል ቀን ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተመሣሣይ ሠዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሣጥኑን ከመከፈቱ በፊት የተወዳደሩባቸውን ሎት 1፣ ሎት 2፣ ሎት 3፣ ሎት 4 ሎት ሎት 5፣ ሎት 6 ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ቀን ተጫራቾች (ህጋዊ ወኪሎቻቸው ባይገኙም ት/ቤቱ ጨረታውን የመክፈት መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን ዕቃዎች በእያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይኖርባቸዋል፡፡
- በጨረታው መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም::
- አሸናፊ ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዢ ፈፃሚው መስሪያ ቤት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያ ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ መይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ት/ቤቱ ዕቃዎችን 20% የመቀነስ ወይም የመጨመር መብቱ የተጠበቀ ነው።
- ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ 5000 (አምስት ሺህ ብር) በባንክ የተረጋገጠ ቼክ ወይም CPO ከሰነዶቻቸው ጋር አያይዘው ማቅረብ አለባቸው።
አድራሻ ፡- አዲሱ ደሴ ሆቴል በተሠራው መንገድ ወረድ ብሎ ልደታ ፀበል መብራቱን ተሻግሮ የሚገኝ ይሆናል፣፣
ስልክ ቁጥር ፡- 0113-69-04-39/0113-69-22-57
የልደታ ሰላም የመ/ደ/ት/ቤት
