የኢትዮጵያ የኬሚካል መሐንዲሶች ማህበር የ2024 እ.ኤ.አ በጀት ዓመት ሐሳብ ለማሠራት እና ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል።
Ethiopian Society of Chemical Engineers (የኢትዮጵያ ኬሚካል መሐንዲሶች ማኅበር)
የኦዲት ሥራ ጨረታ ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ የኬሚካል መሐንዲሶች ማህበር የ2024 እ.ኤ.አ በጀት ዓመት ሐሳብ ለማሠራት እና ኦዲት ለማስደረግ ይፈልጋል፤ ስለሆነም ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን መስፈርቶች የምታሟሉ የሒሳብም ሆነ የኦዲት ሥራ ድርጅቶች መወዳደር የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
- ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ ያለው
- የሙያ ብቃትና በሕጋዊነት ታውቀው በመንግሥት መመዝገቡን የሚገልጽ ማስረጃ የሚያቀርቡ
- የዘመኑን ግብር ከፍለው በ2017 በጀት ዓመት ፍቃዳቸውን ያሳደሱ
- ለሒሳብና ኦዲት ሥራ በቂ የሥራ ልምድና ባለሙያ ያላቸው
- የታክስ መለያ ቁጥር /ቲን / እና የቫት ሰርቲፊኬት ማቅረብ የሚችሉ
- ተወዳዳሪዎችን ለአገልግሎት የምታስከፍሉትን ዋጋ እና ሥራውን ሠርታችሁ የምታስረከቡበትን ጊዜ የሚገልፅ ፕሮፖዛል በማያያዝ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ5 /አምስት/ ተከታታይ የሥራ ቀናት ውስጥ ከዚህ በታች በተጠቀሰው አድራሻ እንድታመለክቱ እናሳስባለን፡፡
አድራሻ ፡- አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ 5 ኪሎ (ኢአ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት) ውስጥ ቢሮ E-109 ወይንም በስልክ ቁጥር 0911433262 በመደወል መጠየቅ የምትችሉ መሆኑን እንገልፃለን፡፡
የኢትዮጵያ ኬሚካል መሐንዲሶች
ማኅበር
