Tender Detail

Tender Details

  • Company SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)
  • Address አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011 5 51 91 00
  • Websitehttps://www.filwuha.gov.et/
  • Deadline05 Mar 2025, 10:00 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Cleaning And Janitorial Equipment

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

SPA SERVICE ENTERPRISE (የፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት)


 

ለሁለተኛ ጊዜ የወጣ የጨረታ ማስታወቂያ

 

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት ከዚህ በታች የተገለጹትን እቃ አገልግሎት ግዥ ለመፈፀም ተጫራቾችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል።

በዚህ መሰረት ፡-

ለሁለተኛ ጊዜ ጨረታ የወጡ የእቃ የአገልግሎት ግዥ

ሎት 1 የፅዳት ዕቃዎች ግዥ ቪም፤ ዲቶል እና ላይለን መጥረጊያ

ሎት 2 የኮረሪማ ግዥ

ሎች 3 የባዮሜትሪክ ማሽን ግዥ

ተጫራቾች የሚከተሉትን መመሪያዎች ማሟላት ተግባራዊ ማድረግ አለባቸው

  1. ተጫራቾች በዘርፉ የተሰማሩበት ሕጋዊና የታደሰ የ2017 ዓ.ም ንግድ ፍቃድ ያላቸውና የዘመኑን ግብር ስለመክፈላቸው ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  2. ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ስለመሆናቸው የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ TIN እና VAT ሰርተፍኬት ያላቸው፤ የገቢዎች ክሊራንስና ጨረታ ለመሳተፍ ከሀገር ውስጥ ገቢ የተሰጣቸውን ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣ ከገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚኒስቴር በአቅራቢዎች ዝርዝር የምዝገባ ፈቃድ የተመዘገቡና የቅርብጊዜ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ።
  3. ማንኛውም ተጫራች ለሎት 1 እና ለሎት 2 የጨረታ ማስከበሪያ 10.000.00 /አስር ሺህ ብር/ እና ለሎት 3 የጨረታ ማስከበሪያ 25.000.00 ሃያ አምስት ሺህ ብር በባንክ በተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ ብቻ ማስያዝ አለባቸው።
  4. ለጨረታ ሰነድ መግዣ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በድርጅታችን አዲሱ ፍልውሃ ሆቴል እንግዳ መቀበያ በመክፈል ከድርጅቱ ግዥ አቅርቦት በድን መሪ ቀርበው የጨረታ ሰነዱን መግዛት ይችላሉ።
  5. ተጫራቾች የሚሰጡት ዋጋ ከቫት በፊትና ከነቫቱ ተብሎ በኢትዮጵያ ብር መገለጽና መሆን አለበት። ተጫራቾች በጨረታ ሰነዶቻቸው ላይ ስማቸውን፤ ሙሉ አድራሻቸውን፣ ፊርማቸውንና ማህተም አሟልተው ማቅረብ አለባቸው።
  6. ጨረታው ከተከፈተ በኋላ በጨረታ ሠነድ ላይ የተሰጠ ዋጋን መለወጥ አይቻልም። ዕቃው የሚቀርብበት ጊዜ፤ ቦታና ዋጋው ፀንቶ የሚቆይበት ጊዜ መገለጽ አለበት። ስለ ዕቃው ዋስትናና የዋስትና ጊዜ በግልጽ መገለጽ አለበት።
  7. ጨረታውን በሚመለከት ለማሸነፍ እንዲረዳዎት ለማንኛውም ኃላፊና ሠራተኛ መደለያ የሰጠ ተጫራች ከጨረታ የሚሰረዝ ሲሆን አሸንፎም ውል ቢዋዋል ውሉ ይሰረዛል።
  8. ድርጅታችን የዋጋ ለውጥ ሳይኖር መጠን ወይም በዋጋ እስከ 25% በመጨመር ወይም 20% ቀንሶ መግዛት እንደሚችል በቅድሚያ መታወቅ ይኖርበታል።
  9. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ከቫት በፊት ወይም ከቫት ጋር በግልጽ በመመላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ የካቲት 26 ቀን 2017 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት ድረስ በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ። ጨረታው ጠዋት በዕለቱ 4:30 ይከፈታል።
  10. ተጫራቾች በሚጫረቱበትን የግዥ አይነት መሠረት የተሟላ የቴክኒካል ሰነድ እና ፋይናንሽያል በተዘጋጀ የጨረታ ሰነድ Bid document/ መሰረት ጨረታ ሰነዳችሁ ማስገባት ይኖርባችኋላ፤ የጨረታው ቴክኒካል ፕሮፖዛል ስነድ ለብቻው የጨረታ ማስከበሪያ ሲፒኦ CPO/ ለብቻው እና ፋይናሽያል ሰነድ ለብቻው በጨረታ ሣጥን ማስገባ አለባቸው።
  11. የጨረታ ሂደቱ የቴክኒክ ግምግማ ድርጅቱ በሚያወጣው መስፈርት መሠረት ለሎት 1 እና ለሎት ቴክኒካል ሠነድ ግምገማ እና ናሙና ጥራት ግምገማ ቤት (40%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምገማ ውጤት (60%) ሲሆን ለሎት 3 ቴክኒካል እስፔስፊክሽን ሠነድ ግምገማ ውጤት (55%) እና የፋይናንሽያል (ዋጋ) ግምግማ ውጤት (45%) ድምር ውጤት ከ100% አሸናፊ የሚለይ መሆኑን ማወቅ አለባችሁ፤ ነገር ግን ቴክኒካል ናሙና ግምገማ እና እስፔስፊኬሽን ሠነድ ግምገማ ያላለፈ ተጫራች ድርጅት ፋይናንሽያል ሰንድ እንደማይከፈት እንዲታወቅ፣ የመገምገሚያ መስፈርቶቹበሚሸጠው የጨረታ ሰነድ ላይ ማየት ይቻላል።

ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ በሙሉ ሆነ በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

ለበለጠ መረጃ ፡- ስልክ ቁጥር 011 5 53 07 67/011 5 15 73 37

 

ፍልውሃ አገልግሎት ድርጅት

 

Save Tender