Tender Detail

Tender Details


በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ከዚህ በታች በሎት ሁለት የቀረቡትን እቃዎች ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል።


 

ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ

ቁጥር 05/2017

 

በሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የትምህርት ቢሮ ለትምህርት ከዚህ በታች በሎት ሁለት የቀረቡትን እቃዎች ግዥ ለማከናወን ሕጋዊ ድርጅቶችን አወዳድሮ በግልጽ ጨረታ ዘዴ መግዛት ይፈልጋል።

ሎት 1. ጥቁር ሰሌዳ ትልቁና ትንሹ

ሎት 2 የህጻናት ፕላስቲክ ወንበርና ጠርጴዛ ፕላስቲክ የወለል ምንጣፍ፣ ፍራሽና ጅባ

ከዚህ በላይ ለተዘረዘሩት በውድድር መስፈርት መሰረት ለመሣተፍ የሚፈልጉ

  1. በመስኩ ህጋዊ የንግድ ፈቃድና የዘመኑን ግብር የከፈሉ እንዲሁም የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥርና ያላቸው መሆን አለባቸው፤ የተጫራቾች የአቅራቢነት ምዝገባ ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው።
  2. ተጫራቾች ዋጋቸውን የሚገልፀውን ሰነድ በታሸገ ፖስታ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ 15ኛው ቀን ከቀኑ 11፡30 ድረስ ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት በአካል በመቅረብ መግዛት አለባቸው፤
  3. የጨረታ ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን በ16ኛው ቀን ከጠዋቱ 3፡00 እስከ 6፡00 ድረስ ብቻ ለዚህ አላማ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው።
  4. ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ16ኛው ቀን 9፡00 ሰዓት ይከፈታል፣ ሆኖም 16ኛው ቀን የስራ ቀን በማይሆንበት ጊዜ በሚቀጥለው የስራ ቀን ከላይ በተጠቀስው ጊዜና ሰዓት የሚከፈት ይሆናል።
  5. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ለ90 ቀን ጸንቶ የሚቆይ ለእያንዳንዱ ሎት ለየብቻ ብር 30,000.00 /ሰላሳ ሺህ / በሲፒኦ ወይም አንኮንዲሻናል ባንክ ጋራንቲ ብቻ በማቅረብ መወዳደር አለባቸው፤
  6. ተጫራቾች ጨረታውን በሚወዳደሩበት ጊዜ በ2 ፖስታ በማሽግ ቴክኒካልና ፋይናንሻል ዶክመንት ለየብቻ በማድረግ የጨረታ ማስከበሪያ በቴክኒካል ውስጥ በማሸግ ማቅረብ አለባቸው። በሁሉም ሎት የእቃው ናሙና የጨረታ ሰነድ በሚገባበት ወቅት መቅረብ አለበት።
  7. ጨረታው ለ3 ወራት /90 ቀናት/ ብቻ ፀንቶ የሚቆይ ይሆናል።
  8. የጨረታ ሰነድ የማይመለስ ብር 200.00 /ሁለት መቶ ብር/ በመክፈል ከግ/ፋ/ን/አስ/ር ዳይሬክቶሬት ማግኘት ይቻላል።
  9. ቢሮው ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።

 

ማሳሰቢያ ፡- ሽያጩ ቫትን ጨምሮ ከብር 20,000.00 /ሃያ ሺህ ብር/ በላይ ለሆነው ግዥ 50% ቫት ቀንሰን የምናስቀር መሆኑን እንገልፃለን።

ለበለጠ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 046 212 4307

 

የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ትምህርት ቢሮ

 

Save Tender