በልደታ ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የአዲስ ፍሬ የመጀ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
የአዲስ ፍሬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
ለ2ኛ ጊዜ የወጣ ግልጽ የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር 010/2017 ዓ.ም
በልደታ ከፍለ ከተማ ወረዳ 9 ትምህርት ጽ/ቤት ስር የሚገኘው የአዲስ ፍሬ የመጀ ደ/ት/ቤት ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዕቃዎች አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡
ሎት 1- የደንብ ልብስ፣ የሰራተኞች ጥቅማ ጥቅምና የደንብ ልብስ ስፌት፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000
ሎት 2- አላቂ የቢሮ ዕቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 1000
ሎት 3- አላቂ የህክምና ዕቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 750
ሎት 4- አላቂ የትምህርት እቃዎች መግዣ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000
ሎት 5- አላቂ ዕቃዎች፣ የፅዳት ዕቃዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000
ሎት 6- ለተለያዩ መሳሪያዎች፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 800
ሎት 7- ለፕላንት ማሽነሪ፤ የጨረታ ማስከበሪያ ብር 2000
ሎት 8- ለፈርኒቸር/የቢሮ ዕቃዎች የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000
ስለሆነም:-
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ዘወትር በሥራ ሰዓት በአዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት በመቅረብ በማይመስስ ብር 50 /ሃምሳ/ በሎት መግዛት ይችላሉ፡፡ እንዲሁም ለጥቃቅን እና አነስተኛ ደርጅቶች የድጋፍ ደብዳቤ በማምጣት በነፃ መውሰድ ይችላሉ፡፡
- ተጫራቾች ሀ/ በዘርፉ የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው
ለ/ በመንግስት ግዢ ኤጀንሲ በአቅራቢነት የተመዘገቡ
ሐ/ በተጨማሪ እሴት ታክስ የተመዘገቡና ቲን ነምበር ማቅረብ የሚችሉ
- በየሎት በተቀመጠው መሰረት የጨረታ ማስከበሪያ ብር መጠን በሲፒኦ በአዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት በማሰራት ከሰነዱ ጋር ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ በጨረታ ሰነድ ውስጥ በሚገኘው የዋጋ ማቅረቢያ ላይ በመሙላት በታሸገ ኤንቨሎፕ ይህ ጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 / አስር/ ተከታታይ የስራ ቀናት ውስጥ በአዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት የጨረታ ሳጥን ውስጥ ማስገባት አለባቸው::
- ለጨረታ ከቀረቡት እቃዎች ዝርዝር ውስጥ ት/ቤቱ እስከ 20 በመቶ ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት መብቱ በሕግ የተጠበቀ ነው::
- የጨረታ አሸናፊ ድርጅት ያሸነፈበትን ንብረት በራሱ ትራንስፖርት የት/ቤት ዕቃ ግምጃ ቤት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ በወጣ በ10ኛው የሥራ ቀን 10፡00 ሰዓት ተዘግቶ የጨረታው ሳጥን በዕለቱ 10፡30 ሰዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በት/ቤቱ መምህራን ማረፍያ ይከፈታል፡፡ የጨረታው መዝጊያና መክፈቻ ቀን የሥራ ቀን ካልሆነ በሚቀጥል የስራ ቀን ከላይ በተጠቀሰው ተመሳሳይ ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች ጨረታው ከመከፈቱ በፊት ለሚወዳደሩበትና ናሙና ለሚያቀርቡባቸው የዕቃ ዓይነት ከመሥርያ ቤታቸው በቀረበ አስፔስፊኬሽን መሰረት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
- ት/ቤቱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል መሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- የአዲስ ፍሬ የመጀ/ደ/ት/ቤት 5ኛ ፖሊስ
ጣብያ ወረድ ብሎ ልዩ ስሙ ስላሴ ወፍጮ ቤት ገባ ብሎ
ለተጨማሪ መረጃ ስልክ ቁጥር ፡- 0115-51-58-61/ 0118-68-56-98
የአዲስ ፍሬ የመጀመሪያ ደረጃ ት/ቤት
