Tender Detail

Tender Details

  • Company በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት
  • Address ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ : አዲስ አበባ ፡ ኢትዮጵያ, Phone: 011-1-23-43-69
  • Website
  • Deadline27 Feb 2025, 4:30 AM
  • magazine
  • Bid Document PriceNot stated in the notice
  • Bid SecurityNot stated in the notice
  • opening dateNot stated in the notice
  • Categories Office Supplies And Services

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር እቃ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት


 

የጨረታ ማስታወቂያ

የጨረታ ማስታወቂያ ቁጥር 002/2017

 

የጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ፋ/ጽ/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት ለ2ኛ ዙር እቃ አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ የቢሮ መገልገያ ቁሳቁሶች እና የአገልግሎት ግዥዎችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡

1) ሎት 01/ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች

2) ሎት 02/ የጽዳት ዕቃዎች

3) ሎት 03 የደንብ ልብስ ዕቃዎች እና የተለያዩ የዲኮር ጨርቅ እና የዲኮር እቃዎች

4. ሎት 04 የቋሚ እቃዎች

5) ሎት 05/ የመስተንግዶ ፣ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና እና የመኪና ጎማ በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡ በመሆኑም በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች የሚከተሉትን ሁኔታዎች በቅድሚያ ማሟላት ይኖርባቸዋል፡-

  • ተጫራቾች በተሰማሩበት የስራ መስክ የዘመኑን ግብር ለመክፈላቸው እና የታደሰ የንግድ ፍቃድ የአቅራቢነት ሊስት ማስረጃ ማቅረብ ይኖርባቸዋል
  • ተጫራቾች በጥቃቅንና አነስተኛ የተደራጁ ከሆነ የሚወዳደሩት በሚያመርቱት እቃ ወይም ተጨማሪ እሴት ለጨመሩት እቃ ሲሆን ከዚህ ውጭ ለሆኑ እቃዎች የሚወዳደሩት እንደማንኛውም ተጫራች ሰነድ በመግዛትና ሲፒኦ (CPO) በማስያዝ ይሆናል፡፡ ተወዳዳሪዎች በሚያመርቱት እቃ ሲወዳደሩ እና ካደራጃቸው መስሪያ ቤት የድጋፍ ደብዳቤ ሲያመጡ ልዩ ድጋፍ ይደረግላቸዋል፡፡
  • የመንግስት የግዥ ጨረታ ላይ ለመሳተፍ የሚያስችል የተሟላ ማስረጃ ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ ለመሆናቸው ማስረጃ ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • የጨረታ ሰነዱን በጉለሌ ክ/ከተማ ከወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር12 በመምጣት ሰነዱን በማይመለስ ለእያንዳንዱ ሎት ብር 250 (ሁለት መቶ ሃምሣ ብር ብቻ) በመግዛት መውሰድ ይችላሉ
  • የጨረታውን ሰነድ ኦርጅናል እና ኮፒ ሞልተው ማቅረብ አለባቸው፡፡
  • ጨረታው ጋዜጣ ከወጣበት ቀናት አንስቶ ለ10 ተከታታይ የስራ ቀናት ይቆያል፡፡
  • ጨረታው በአስረኛው ቀን 10፡30 ሰዓት ላይ ታሽጎ በአስራ አንደኛው ቀን 3:30 ተጫራቾች ወይም ሕጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት 4ኛ ፎቅ ላይ ቢሮ ቁጥር 12 ይከፈታል።
  • ተጫራቾች ከጨረታው ሰነድ ውጪ ተሞልቶ ያመጡት ሰነድ ተቀባይነት የለውም
  • መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው።
  • ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ማሲያዝ የሚኖርባቸው ሲሆን ይኸውም
  • ሎት 01/ አላቂ የቢሮ ዕቃዎች የሚሆን ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ሎት 02/ የጽዳት ዕቃዎች የሚሆን ብር 5.000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ሎት 03/ የደንብ ልብስ ዕቃዎች እና የተለያዩ የዲኮር ጨርቅ እና የዲኮር እቃዎች የሚሆን ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ሎት 04/ የቋሚ እቃዎች የሚሆን ብር 10,000.00 (አሥር ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ሎት 05/ የመስተንግዶ ፡ የኤሌክትሮኒክስ ጥገና የመኪና ጎማ የሚሆን ብር 5,000 (አምስት ሺህ ብር ብቻ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡ እንዲሁም የጨረታ አሸናፊ ከሆኑ በኋላ የውል ማስከበሪያ 10% ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
  • ተጫራቾች ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ዕቃዎች ናሙና የማቅረብ ግዴታ ይኖርባቸዋል የሚቀርቡትም ናሙናዎች ተፈተው የሚታዩ መሆናቸውን ተጫራቾች ማወቅ አለባቸው፡፡
  • ተጫራቾች በአማራጭ ገበያ መጠቀም የተከለከለ ነው ::
  • ተጫራቾች ያሸነፉባቸውን ዕቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ወረዳ ግቢ ድረስ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
  • መ/ቤቱ ካሸናፊው ድርጅት ያሸነፉበትን ዋጋ መጠን እና ብዛት 25% ተጨማሪ ትዕዛዝ መጠየቅ የሚችል መሆኑ መታወቅ አለበት፡፡
  • መ/ቤቱ ከውል በፊት እንደ አስፈላጊነቱ የእቃውን ብዛት 20% መጨመር ወይም መቀነስ እንደሚችል መታወቅ አለበት፡፡

ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡-

አድራሻ ፡- ስድስት ኪሎ ከፍ ብሎ ስብሰባ ማዕከል አጠገብ ወደ ሐምሌ19 መናፈሻ ሳይደርስ 50 ሜትር ገባ ብሎ

ስልክ ቁጥር ፡- 011-1-23-43-69 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡

 

በጉለሌ ክ/ከተማ የወረዳ 2 ፋይናንስ ጽ/ቤት

 

Save Tender