በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
የግልጽ ጨረታ ማስታወቂያ
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ለ2017 በጀት ዓመት የሚያስፈልጉ እቃዎችን በግዥ መለያ ቁጥር 02/2017 ማለትም
- ሎት 01 አላቂ የቢሮ እቃ እና ህትመቶች ፣
- ሎት 02 ቋሚ እቃ፣
- ሎት 03 አላቂ የትምህርት እቃ፣
- ሎት 04 የጽዳት እቃዎች ፤
- ሎት 05 የደንብ ልብስ፣
- ሎት 06 ጥገና በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል፡፡
ስለሆነም በጨረታው ለመሳተፍ የምትፈልጉ
- ለሎት 01 የጨረታ ማስከበርያ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር)
- ለሎት 02 የጨረታ ማስከበርያ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር)
- ለሎት 03 የጨረታ ማስከበሪያ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር)
- ለሎት 04 የጨረታ ማስከበርያ ብር 4000 (አራት ሺህ ብር)
- ለሎት 05 የጨረታ ማስከበርያ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር )
- ለሎት 06 የጨረታ ማስከበርያ ብር 3000 (ሶስት ሺህ ብር) በባንክ በተረጋገጠ ሰነድ (CPO) ከጨረታው ሰነድ ጋር በፖስታ በማሸግ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
ብቃት ያላቸውንና በመስኩ የተሰማሩ ተጫራቾችን አወዳድሮ ግዥ መፈጸም ይፈልጋል፡፡
በዚህም መሰረት ፡-
- በጨረታው ለመወዳደር ፍላጎት ያላቸው ተጫራቾች የታደሰ ንግድ ፍቃድ ያላቸው፣የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ የቲን እና የቫት ተመዝጋቢ የሆኑና የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ በዘርፉ የተሰማሩ መሆን አለባቸው፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ብር 200 (ሁለት መቶ ብር) ብቻ በመክፈል ሰነዱን ፋይናንስ ቢሮ ቁጥር 2-02 ቀርበው መግዛት ይችላሉ፡፡
- ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በጋዜጣ ታትሞ አየር ላይ ከዋለበት ቀን ጀምሮ እስከ 10ኛው ቀን እስከ 11፡30 ድረስ አየር ላይ ዉሎ በ11ኛዉ ቀን ከጠዋቱ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ጨረታው ይከፈታል፡፡
- ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዳቸውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ማስታወቂያው ከወጣበት እለት ጀምሮ ለተከታታይ 10 የስራ ቀናት ፋይናንስ ክፍል ቢሮ ቁጥር 2-02 ለጨረታ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ተጫራቾች የጨረታ ሳጥን ከመከፈቱ በፊት ለተወዳደሩባቸው ለሎት 01 ፤ ለሎት 03፣ ለሎት 04፣ እና ለሎት 05፤ ናሙና ማቅረብ አለባቸው፡፡ ለሎት 02 ማለትም ለቋሚ እቃ በመስሪያ ቤቱ የፍላጎት መግለጫ መሰረት ብቻ ይሆናል፡፡
- ተጫራቾች የሚወዳደሩባቸውን እቃዎች ለያንዳንዱ ከቫት ጋር ያለውን ዋጋ ማስቀመጥ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- የዘገየ ጨረታና በጨረታ መክፈቻ ላይ ያልተነበበ ጨረታ ተቀባይነት የለውም
- አሽናፊ ተጫራቾች ያሸነፈባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ግዥ ፈጻሚው መስሪያ ቤቱ ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መስሪያቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ ፡- በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ወረዳ 01 ሃይሌ ጋርመንት አደባባይ ወደ ላይ ከፍ ብሎ ፡፡ ለተጨማሪ መረጃ ፡- በስልክ ቁጥር 011 471 3190/91 ደውለው መጠየቅ ይችላሉ፡፡
በን/ስ/ላ/ክ/ከ/ ለቡ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
